ኒው ዮርክ መብራት መጣ

ኒውዯርክ ጨለማ ውጧት ነበር ያደረችው Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ የትራፊክ መብራቶች ባለመስራታቸው የትራፊክ መተረማመስ አስከትለው ነበር።

ቅዳሜ ለታ ማታ መብራት በኒው ዮርክና አካባቢው ድርግም ብሎ ጠፋ። ሊፍት ውስጥ የነበሩ ሰዎች እዚያው ተከርችሞባቸው ዋሉ። ባቡር ባለበት ቆመ። የዓለም ዋና ከተማ ተደርጋ የምትታሰበው ዘናጯ ኒውዮርክ እንቅስቃሴዋ ሁሉ ተገታ።

ቢያንስ 70ሺህ የሚሆኑ ቤቶችና የንግድ ተቋማት በዚህ ምክንያት ከባድ ችግር ውስጥ ገብተዋል። በተለይም ሕዝብ በሚበዛባት ማንሃታን ብዙዎች በመብራት መጥፋት ምክንያት ፍዳቸውን ሲያዩ ነበር።

ይህ የመብራት መጥፋት ለአምስት ሰዓታት የዘለቀ ነበር።

ከፀሐይ ኃይል ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የሚጥሩ ወንድማማቾች

ከበለስ ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የምትመራመረዋ ኢትዮጵያዊት

ረጅሙ የአውሮፕላን በረራ ስንት ሰዓት ይፈጅ ይሆን?

ይህ የቅዳሜ ማታው የመብራት መጥፋት ድሮ በ1977 በተመሳሳይ መብራት ጠፍቶ ብዙ ውንብድናና ዝርፍያ በተፈጸመበት ዕለት መሆኑ ብዙዎችን አስገርሟል። የ1977 መብራት መጥፋት ኒው ዮርክን በጨለማ ከማቆየቱም በላይ ሰዎች ከሕግ ውጭ ወጥተው በርካታ ቤቶችን ሲያቃጥሉና ያገኙትን ሲዘርፉ የዋሉበት ዘመን በመሆኑ በታሪክ የሚታወስ ነው።

ኒው ዮርክን ለድቅድቅ ጨለማ የዳረጋት ችግር ምን እንደሆነ እስካሁንም በውል አልታወቀም። ሆኖም ምንጩ በአንድ ንዑስ ማስተላለፊያ መበላሸት ሳይሆን እንዳልቀረ ይገመታል።

ከኒው ዮርክ 5ኛው ጎዳና እስከ ሀዲሰን ሪቨር ያዳረሰው ጨለማ የትራፊክ ፍሰቱን በማስተጓጎሉ መንገዶች ቅጥ ባጣ ሁኔታ በመኪና ጡሩንባ ሲታወኩ ነበር።

የኤሌክትሪክ ኃይል በፈረቃ መከፋፈሉ መቅረቱ ተገለፀ

ከንቲባ ቢል ዴ ብላሲዮ ለኒው ዮርክ ፖሊስ እንዳረጋገጡት የመብራት መጥፋቱ ምንም ዓይነት አሻጥር ያለበት ነገር ሳይሆን መካኒካዊ ችግር የፈጠረው ነው።

ለቅዳሜ ማታ ትዕይንት ሊያሳዩ የነበሩ ቲያትር ቤቶችም ደንበኞቻቸውን ይቅርታ እየጠየቁ ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ተገደዋል።

በማዲሰን ስኩዌር ጋርደን የሙዚቃ ድግስ ልታቀርብ ቀን ተቆርጦላት የነበረችው ዝነናዋ ጄኔፈር ሎፔዝ መብራት በመጥፋቱ ምክንያት ዝግጅቷ መሰረዙ እጅግ እንዳሳዘናት ተናግራለች።

ተያያዥ ርዕሶች