የጋዜጠኛዋ መገደል ለምን የዓለም መነጋገሪያ ሆነ?

ሆዳን ናላያህ

አብዛኛዎቹ መገናኛ ብዙኃን ሶማሊያን የጦርነት ቀጣና፣ ድርቅ እና ረሃብ የማይለያት፣ የእርዛትና ጥማት ተመሳሌት፣ እንዲሁም የእርስ በርስ እልቂት ምሳሌ አድርገው ነው የሚስሏት። አንዲት ሴት ግን ይህን ለመቀልበስ ተነሳች።

ይህቺ ሴት ሆዳን ናላያህ ትባላለች። ትውለደ ሶማሊያዊ የሆነችው ሆዳን ከ6 ዓመቷ ጀምሮ ካናዳ ነው ያደገችው። ይሁን እንጂ ልቧ ሁሌም ሶማሊያ ነው ያለው።

የሶማሊያን ውበት፣ መልካም ገጽታና የሕዝቧን ትስስር ለተቀረው ዓለም ለማሳየት ቆርጣ የተነሳች ሴት በመሆኗ ከዓመት በፊት ከካናዳ ወደ ሶማሊያ ተመለሰች።

በሶማሊያ በአንድ ሆቴል ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 26 ሰዎች ሞቱ

ኒው ዮርክ መብራት መጣ

ትራምፕ የኢራን ኒውክሌር ስምምነትን ያፈረሱት ''ኦባማን ለማበሳጫት'' ነው

ዓላማ ያደረገችው በዓለም ላይ እንደ አሸዋ የተበተኑ ሕዝቦቿን በተለይም ውጭ አገር ያደጉ የሶማሊያ ወጣቶችን ማነቃቃትና አገራችን እንዲወዱ ማድረግ ነበር።

"ሶማሊያ ጦርነት ብቻ አይደለም ያለው...፣ሕይወት አለ፣ ፍቅር አለ..."

ሆዳን ዕሮብ ዕለት ከኪሰማዮ ከተማ ወጣ ብሎ ወደ ሚገኝ ስፍራ በመጓዙ አሳ እያጠመዱ ለገብያ ስለሚያቀርቡ ወጣቶች እና ስለአካባቢው ውብ ተፍጥሮ በትዊተር ገጿ ብዙ ብላ ነበር።

አርብ 'ለታ ተገደለች

ይቺ በመላው ዓለም የሶማሊያ አምባሳደር ሆና ትታይ የነበረችው ናላያህ አርብ 'ለታ በደቡባዊ ሶማሊያ ኪስማዮ ከተማ ባረፈችበት አንድ ሆቴል ውስጥ በድንገት ተገደለች።

በርካታ ሶማሊያዊያንና በተለይም የርሷን ሥራዎች የሚከታተሉ፣ የርሷን ተስፋ የሚመገቡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ታዳሚዎቿ እጅግ አዘኑ።

አልሸባብ ኃላፊነቱን በወሰደበት ጥቃት እሷና ባለቤቷን ጨምሮ 26 ሰዎች ተገድለዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመበት አሳሰይ ሆቴል የአገር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎችና ፖለቲከኞች መጪውን ምርጫ ተአማኒና ዲሞክራሲያዊ ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ ለማመቻቸት እየተወያዩ ነበር።

ናላዬህ 43ኛ ዓመቷ ላይ ነበረች። ሁለት ልጅችም ነበሯት። "በተገደለችበት ወቅትም ነፍሰጡር ነበረች" ብለዋል ቤተሰቦቿ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ።

ናላያህ በሰሜን ሶማሊያ ላስ አኖድ በምትባል ከተማ ብትወለድም ያደገችው ግን ካናዳ ውስጥ ነው።

በአንድ ወቅት ለቶሮንቶ ለሚገን አንድ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገረችው አባቷ የቀድሞ የሶማሊያ ዲፕሎማት የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን በካናዳ የመኪና ማቆሚያ አስተናባሪ ሆነው በመሥራት ላይ ናቸው።

ካናዳ ሳለች በብሮድካስት ጆርናሊዝም ሁለተኛ ዲግሪዋን እንደያዘች ነበር የራሷን ቴሌቪዥን የጀመረችው።

በቢቢሲ የምትሰራዋ ጓደኛዋ ፋርሃን ናላያህን «ብሩህ አእምሮና ውብ ነፍስ የታደለች» ስትል ትገልጻታለች።

ብዙዎች ትውልደ ሶማሊያዊያን ወደ አገራቸው መትመም የጀመሩት በርሷ አነቃቂ የጋዜጠኝነት ሥራዎች ምክንያት ነበር።

የርሷ መገደል ይበልጥ ሶማሊዊያን እንዲቀራረቡና የቆመችለትን ዓለማ ወደፊት እንዲገፉ ነው የሚያደርጋቸው ትላለች ጓደኛዋ።

በአንድ ወቅት ሟች ናላያህ ወደፊት በምን እንድትታወስ እንደምትፈልግ ተጠይቃ።

"እኔ ገንዘብም ዝናም ብዙም አይማርከኝም፤ የሶማሊያን አንድነት ማየት ነው ለኔ ትልቁ ህልም...ያን ለማሳካት ነው የምኖረው" ስትል ተናግራ ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች