ኦብነግ በአዲስ አበባ ቢሮ ከፈተ

ኦብነግ የተኩስ አቁም አወጀ Image copyright ONLF

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር-ኦብነግ ትናንት በአዲስ አበባ ቢሮውን ከፈተ።

ፓርቲው በይፋዊ የትዊተር ገጹ እንዳሰፈረው ትናንት ቢሮውን በመዲናዋ ሲከፍት የፓርቲው አመራሮች፣ መንግሥት ተወካዮችን ጨምሮ የውጪ ሃገራት አምባሳደሮችም በስነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ኦብነግ በአዲስ አበባ የነበው ቢሮ ከ25 ዓመታት በፊት በመንግሥት ጫና እንዲዘጋ መደረጉን አስታውሷል።

ኦብነግ የተኩስ አቁም አወጀ

ልዩ ፖሊስን ማን መሰረተው?

አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ኦብነግ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እየተደራደረ ነው

ለዓመታት በምሥራቅ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሲንቀሳቀስ የነበረው ኦብነግ፤ በመንግሥት በኩል ለንግግርና ለሰላም እየተወሰዱ ያሉትን አዎንታዊ እርምጃዎችን እቀበላለሁ በማለት ነሐሴ 6 2010 ዓ.ም. የተኩስ አቁም ማወጁ ይታወሳል።

የኦብነግ ከፍተኛ አመራሮች ወደ አዲስ አበባ የገቡት የዛሬ ዓመት ገደማ ነበር።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኦብነግን ጨምሮ ኦነግ እና ግንቦት 7ን ሽብርተኛ መባላቸው ይሰረዝ ዘንድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት የላከለትን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከተወያየበት በኋላ ማጽደቁ ይታወሳል።