አል ሻባብ የጎሳ መሪዎችን አስጠነቀቀ

የአል ሻባብ ታጣቂዎች Image copyright AFP

የሶማሊያው ታጣቂ እስላማዊ ቡድን አል ሻባብ ለፓርላማ አባል የሚሆኑ እጩዎችን አቅርበዋል ያላቸውን የጎሳ መሪዎች "ከሃዲዎች" በሚል መግለጫ አወጣ።

"ለከሃዲው የሶማሊያ ምክር ቤት አባልነት እጩዎችን የሰየሙ የጎሳ መሪ የተባሉት ግለሰቦች ኢአማኒ መሆናቸውን በግልጽ በማስመስከር የእስልምና እምነታቸውን ዋጋ አሳጥተውታል" ሲል አፍቃሪ አልሻባብ በሆነው ድረ ገጽ ላይ ቡድኑ ያወጣው መግለጫ ያመለክታል።

ከአል ቃኢዳ ጋር ትስስር እንዳለው የሚነገርለት አል ሻባብ ቀደም ሲል ሲቆጣጠራቸው ከነበሩ አብዛኞቹ ዋነኛ የሶማሊያ ከተሞች ተገፍቶ የወጣ ቢሆንም አሁንም ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ነው።

የጋዜጠኛዋ መገደል ለምን የዓለም መነጋገሪያ ሆነ?

በሶማሊያ በአንድ ሆቴል ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 26 ሰዎች ሞቱ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ

አል ሻባብ በመግለጫው የጎሳ መሪዎቹ ፈጸሙት ላለው ሐጢያት በ45 ቀናት ውስጥ 'ንስሐ' እንዲገቡ ካልሆነ ግን የጂሃዳዊ ቡድኑ ኢላማ በመሆን እንደሚገደሉ አሳውቋል።

አልሻባብ ጨምሮም የጎሳ ሽማግሌዎች ክልላዊ አስተዳደርን በመመስረቱ ሂደት ውስጥ እንዳይሳተፉም አስጠንቅቋል።

ይህ ማስጠንቀቂያ በእስላማዊ ቡድኑ የወጣው ጁባላንድና ጋልሙዱግ በተባሉት የሶማሊያ ግዛቶች ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ሊካሄድ በታሰበበት ጊዜ ነው።

ቀደም ሲል በተካሄዱ የሶማሊያ ክልላዊ ምርጫዎች ላይ የቀረቡ በርካታ ዕጩዎች በአል ሻባብ መገደላቸው ይታወሳል።

ታጣቂው እስላማዊ ቡድን በተባበሩት መንግሥታት የሚደገፈውን የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥትን ለመጣል እየተፋለመ ሲሆን፤ በተለያዩ ቦታዎች ተከታታይ ጥቃቶችን ሲፈጽም ቆይቷል።