ኦሌ ጉና ሶልሻየር፡ አራተኛ ሆኖ መጨረስ በቂ አይደለም

ኦሌ ጉና ሶልሻየር Image copyright Getty Images

ኦሌ ጉና ሶልሻየር ማንችሰተር ዩናይትድ በቀጣዩ የውድድር ዘመን ''አራተኛ ሆኖ ከመጨረስ በላይ ነው የሚያልመው'' ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጡ።

የ46 ዓመቱ አስልጣኝ ማንችስተር ዩናይትድን ከጆሴ ሞሪኒሆ መቀበላቸው ይታወሳል።

ሶልሻየር የቀያይ ሴጣኖቹ ቋሚ አሰልጣኝ ሆነው ከመሾማቸው በፊት ካደረጉት 19 ጨዋታዎች 14ቱን ማሸነፍ ችለው ነበር። ኦሌ ቋሚ አሰልጣኝ ሆነው ከተሾሙ በኋላ ግን ካደረጓቸው 10 ጨዋታዎች ሙሉ ነጥብ መሰብሰብ የቻሉት ከሁለት ጨዋታዎች ብቻ ነው።

ዩናይትዶች አዲሱ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት የሚከናወኑ ጨዋታዎችን ለማድረግ አውስትራሊያ የሚገኙ ሲሆን፤ ኦሌ ጉና ሶልሻየር ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ የቀጣዩ የውድድር ዘመን እቅዳቸውን ጨምሮ ስለ አሌክሲስ ሳንቼዝ እና ፖል ፖግባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

"እንዴት ለሴት ልጅ የወንዶች ክለብ ይሰጣል?' ተብሎ ነበር" መሠረት ማኒ

ኦሌ ጉና ስለቀጣዩ የውድድር ዓመት ሲናገሩ፤ በሊጉ ሰንጠረዥ የመጀመሪያዎቹ አራት ውስጥ ለመጨረስ ከሚደረገው ጥረት በላይ ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።

"ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች አሉን በተጨማሪም ለቡድኑ በትክክል የሚመጥኑ ተጨዋቾችን በማስፈረም ከምንፈልገው ቦታ ላይ መድረስ እንችላለን። የሚጠበቅብን ወጥ የሆነ አቋም ላይ መገኘት መቻል ነው። በየቀኑ ጠንክረን እየሰራን ከእቅዳችን ዘንበል ማለት የለብንም።"

የዩናይትዶቹ አሰልጣኝ ኦሌ ጉና ሶልሻየር ለቡድኑ ስኬት የፖል ፖግባ አሰተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ። ኦሌ ''ፖል ድንቅ ተጫዋች እና የሚደንቅ ሰው። በሞልዴ ክለብ እያለሁ፤ 'ፖል በቡድን ውስጥ ካለ፤ በእሱ ላይ በመመስረት ቡደን መመስረት ይቻላል' እል ነበር። አሁንም ተመሳሳይ እምነት ነው ያለኝ። የዩናትድ ደጋፊዎች የቡድናቸውን አጨዋወት ያውቃሉ። ፖልን የሚተቹ ብዙ ቢሆንም በበርካቶች ግን ይወደዳል።

«የኔ ትውልድ ታሪክ እንደሚሠራ እምነት አለኝ» ሎዛ አበራ

ከአርሰናል ወደ ማንችስተር የተዘዋወረው አሌክሲስ ሳንቼዝ በክለቡ ውስጥ ትልቅ ስም እና ክፍያ ካላቸው ቀዳሚ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው። ይሁን እንጂ ሳንቼዝ ወደ ማንችስትር ከተዘዋወረ በኋላ በክለቡ ወጥ አቋም ማሳየት አልቻለም።

''የአሌክሲስን አቅም ሳስብ ትልቅ እረፍት ይሰጠኛል። ማድረግ የሚችለውን እናውቃለን። ምን ማድረግ እንዳለብን ነው መለየት ያለብን። ምክንያቱም አሌክሲስ በቀላሉ 20 ጎሎችን ሊሰጠን የሚችል ተጫዋች ነው። በኮፓ አሜሪካ ላይ ይህን አይተናል። ወጥ አቋም ማየት አልቻለንም በተጨማሪም ጎዳቶች ሲያጋጥሙት ነበር። ወደ ድንቅ አቋሙ ይመለሳል ብለን እናስባለን''

በማንችሰተር ዩናይትድ ቤት ውስጥ የተጫዋቾች ዝውውር ስትራቴጂን በሚመለከት ''እዚህ የማልፈልጋቸው ተጫዋቾች የሉም። አሁንም አንድ ወይም ሁለት ተጫዋቾችን ለማስፈረም እየሞከርን ነው። ክለቡን የሚለቁ ተጫዋቾች ካሉ እነሱን ለመተካት ሌሎች ተጫዋቾችን የማስፈረሙ ስራ ይኖራል'' ሲሉ መልሰዋል።

ኦሌ ጉና ስለ ወጣቱ ሜይሰን ግሪንውድ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ''ተፈጥሯዊ የእግር ኳስ ክህሎት ያለው ተጫዋች ነው። በቀኝ እግሩም ሆነ በግራ እግሩ ጎል ያስቆጥራል። ሁለቱንም እግሮቹን በሚገርም ብቃት ይጠቀማል። ቀኝ ወይም ግራኝ ስለመሆኑ እርሱ እራሱ የሚያውቀው አይመስለኝም። መቶ በመቶ እርግጠኛ የምሆነው በዚህ የውድድር ዘመን ጎሎችን ያስቆጥራል''

ከቀድሞ የክለቡ አልጣኝ ሰር አሌክ ፈርጉሰን ጋር ስላላቸው ግነኙነት የተጠየቁት ኦሌ ''ለ14 ዓመት ከፈርጉሰን ጋር አብሬ ሰርቻለሁ። አብዛኛው የእግር ኳስ ህይወቴ ከእርሱ ጋር ነው ያሳለፍኩት። ከፈርጉሰን ብዙ ትመሬያለሁ ይህ እውነት ነው። ከጨዋታ በኋላ አልፎ አልፎ እንነጋገራለን፣ የጽሁፍ መልዕክት እንላላካለን ከዚህ ውጪ ሌሎች ብዙ የሚባሉት ነገሮች ግን ስህተት ናቸው።

ያለእድሜ ጋብቻን በእግር ኳስ የምትታገለው ታዳጊ

ኦሌ ጉና በስተመጨረሻም ቡድን እንደ አዲስ ማዋቀር ጊዜ የሚወስድ መሆኑን በመጠቀስ የዩናይትድ ደጋፊዎች ትዕግስት እንዲኖራቸው ጠይቀዋል።

ተያያዥ ርዕሶች