ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የኢራንን ሰው አልባ አውሮፕላን መታ መጣሏን ተናገሩ

የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከብ Image copyright AFP/Getty Images

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ባህር ኃይል የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላንን በስትራይት ሆርሙዝ አካባቢ መታ መጣሏን ተናገሩ።

ሐሙስ ዕለት የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን የአሜሪካ የጦር መርከብን በ914 ሜትር ርቀት ቀርቦ እንደነበር የተናገሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የጦር መርከቡም "ራሱን የመከላከል እርምጃ" ወስዷል ብለዋል።

ኢራን በበኩሏ ሰው አልባ አውሮፕላን ስለመጥፋቱ መረጃ የለኝም ስትል ተናግራለች።

ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ኢራን የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላንን መታ መጣሏ ይታወሳል።

ክልልነት ለጠየቀው ሁሉ ቢሰጥ ችግሩ ምንድነው?

ኢራን እሁድ ዕለት የሌላ አገር "የነዳጅ ጫኝ መርከብና" 12 ሠራተኞቹን በገልፍ በኩል ነዳጅ በሕገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ በቁጥጥር ስር ማዋሏን ተናግራ ነበር።

ኢራን ከግንቦት ወር ጀምሮ በአሜሪካ የዓለም እቃ ጫኝ መርከቦች በከፍተኛ ሁኔታ በሚንቀሳቀሱበት የባህር ክልል የነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት በማድረስ ስትከሰስ ነበር። ክሱን ግን ቴህራን አስተባብላለች።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሁለቱ አገራት መካከል የሚፈጠሩ ምልልሶችና እሰጥ አገባዎች በክልሉ ጦርነት ይቀሰቅሳል የሚል ስጋት በብዙዎች ዘንድ ፈጥሯል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ ላይ የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን መተው ጥለዋል የተባሉትን የአሜሪካ ጦር መርከብ ባልደረቦችን አደናንቀዋል።

የአዲስ አበባ መስተዳደርና የባላደራው ምክር ቤት

በአዲስ አበባ ቢያንስ 3.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ትራንስፎርመሮች ተሰረቁ

"በግምት 914 ሜትር ተጠግታ የነበረች የኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን ላይ የወሰዱት እርምጃ ራስን መከላከል ነው፤ አውሮፕላኗ በተደጋጋሚ ከአካባቢው እንድትርቅ ቢነገራትም ትዕዛዙን በመተላለፍና የመርከቡንና የሠራተኞቹን ደህንነት አደጋ ላይ በመጣሏ የማያዳግም እርምጃ ተወስዷል" ብለዋል።

ዋሺንግተን ከዚህ አስቀድሞ ኢራን በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸውን ነዳጅ ጫኝ መርከብና ሠራተኞቹን እንድትለቅ ጥሪ አቅርቦ ነበር።

የኢራን ብሔራዊ መገናኛ ብዙኀን የኢራን ሪቮሊውሽነሪ ጋርድን ጠቅሶ፤ ነዳጅ ጫኝ መርከቡ አንድ ሚሊየን ሊትር ነዳጅ በድብቅ እያጓጓዘ ነበር ብሏል።

በኋላም መገናኛ ብዙኀኑ ባወጣው ተንቀሳቃሽ ምስል የኢራን ፈጣን ጀልባ የፓናማ ባንዲራ የምታውለበልብ ሪሀ የተሰኘች ነዳጅ ጫኝ መርከብን ሲከብና ሲያስቆም አሳይቷል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ