በጀርመን በኤርትራዊ ላይ ባነጣጠረ የዘር ጥቃት የግድያ ሙከራ ተደረገበት

ፖሊስ የግድያ ሙከራው በተደረገበት አካባቢ ምልክቶችን አስምሯል Image copyright Reuters

አንድ የ55 ዓመት ጀርመናዊ በመኪና ውስጥ ሆኖ ነው ኤርትራዊውን ለመግደል የሞከረው። ፖሊስ የዘር ጥቃት ባለው በዚህ የግድያ ሙከራ ሦስት ጥይቶች በኤርትራዊው ላይ የተተኮሱ ሲሆን አንድ ጥይት ሆዱ አካባቢ አግኝቶታል፤ ኾኖም ለሕይወቱ አስጊ እንዳልሆነ እየተነገረ ነው። ጥቃት አድራሹና ኤርትራዊውም የቀደመ ትውውቅ እንደሌላቸው ፖሊስ አስታውቋል።

ጥቃት አድራሹ በጥቂት ኪሎ ሜትር ርቀት መኪናው ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል። የራስ ቅሉ በጥይት ተመትቶ መኪናው ውስጥ መገኘቱ ፖሊስ ጥቃት አድራሹ ራሱን እንዳጠፋ እንዲገምት አስችሎታል።

የአልጀሪያዋ ቁንጅና አሸናፊዋ ዘረኝነት እንደማይበግራት ገለፀች

ዘረኝነት ለእናቶች ሞት ምክንያት እየሆነ ነው?

ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለራዕይ

በጀርመናዊው ቤት ውስጥም በርከት ያሉ የጦር መሣሪያዎች ተገኝተዋል።

ምንም እንኳ ጥቃቱ በቀኝ አክራሪዎች የተቀነባበረ እንደሆነ ቢገመትም ፖሊስ ግን ይህን ለማለት የሚያበቃ መረጃ ለጊዜው አላገኘሁም እያለ ነው።

ስደተኞችን በመደገፍ የሚታወቁት እውቁ ጀርመናዊ ፖለቲከኛ ባለፈው ወር ቤታቸው ሳሉ በአንድ አክራሪ ቀኝ ዘመም አባል መገደላቸው በመላው ጀርመን ድንጋጤን ፈጥሮ ቆይቷል።

ስቴፈር ኤርነስ የተባለ የቀኝ አክራሪ ተጠርጣሪ ለፍርድ ቤት እንደተናዘዘው "ለስደተኛ አዛኝና ተቆርቋሪ የነበሩትን ፖለቲከኛ የገደልኳቸው እኔ ነኝ" ብሎ ነበር።

የጀርመን የደኅንነት መዋቅር ስለምን በቀኝ አክራሪዎች ላይ ፈጣን እርምጃ እንደማይወስድ የብዙዎች ጥያቄ ነው።

በሰሜን ምሥራቅ ፍራንክፈርት የተከሰተው የትናንቱ በኤርትራዊው ላይ የደረሰ ጥቃት የዘር ጥቃት ስለመሆኑ ጥርጣሬ አላሳደረም።

የግድያ ሙከራ የተደረገበት ኤርትራዊ ዛሬ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል። ዛሬ ማታም ጥቃቱ በደረሰበት ከተማ የጸረ ዘረኝነት የመታሰቢያ መርሃ ግብር ተሰናድቷል።

ፖሊስ ባወጣው መረጃ በጥቃት አድራሹ መኪና ውስጥ ሁለት መካከለኛ አውቶማቲክ የጦር መሣሪያ የተገኘ ሲሆን ሦስት ሌሎች ሽጉጦች ደግሞ ቤቱ ውስጥ ተገኝተዋል።

ሁሉም ሽጉጦች ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ናቸው።

ጥቃት አድራሹ ቤት ውስጥ ከጦር መሣሪያዎች በተጨማሪ አንድ ደብዳቤ የተገኘ ሲሆን የደብዳቤውን ይዘት ፖሊስ ለጊዜው ይፋ ለማድረግ አልደፈረም።

ተያያዥ ርዕሶች