ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን?

ዱቤ ጅሎ Image copyright Dube Jillo Facebook page

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቴክኒካል ዳይሬክተርነት እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ዱቤ ጅሎ ለኢትዮጵያዊ የመጀመሪያ ነው የተባለውን ሽልማት ሊያገኙ ነው።

የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (አይኤኤፍ) 'ቬተራን ፒን' የሚል ስያሜ ያለው ይህ ሽልማት ዜና ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ከጥቂት ቀናት በፊት እንደደረሳቸው አቶ ዱቤ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ

በታላቁ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ላይ የአበረታች መድኃኒት ምርመራ ሊካሄድ ነው

ይህንን ሽልማት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊ አግኝቶት እንደማያውቅም አቶ ዱቤና ሌላ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተጠባባቂ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ብስራት ገልፀዋል።

ሽልማቱ ከዚህ ቀደም አትሌት የነበሩና ለስፖርቱ ዕድገትና ልማት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሚሰጥ ሲሆን ከዚህም በፊት ኬንያዊው አትሌት ፖል ቴርጋት ተሸልሟል።

የአፍሪካው አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን መርጦ ወደ ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመላክ የሽልማቱ ሂደት ይከናወናል።

ሽልማቱ መስከረም ወር ላይ ዶሃ በሚዘጋጀው የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ሻምፒዮን በመስከረም ወር የሚሰጥ ይሆናል።

ታይላንዳዊው ቦክሰኛ በውድድር ሳቢያ ሕይወቱ አለፈ

ሽልማቱን ያገኙበት ምክንያት

ሽልማቱ ዕውቅና መስጠት ነው የሚሉት አቶ ዱቤ "ከአስር አመታት በላይ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት አስተዋፅኦ ላደረግኩት የሚበረከት ነው። "በወቅቱም ውጤታማ አፈፃፀሞች ላሳየሁባቸው እውቅና መስጠት ነው" ብለዋል።

በሽልማቱ መደሰታቸውን ገልፀው የበለጠ ለስራ እንደሚያነሳሳቸው ይናገራሉ።

"ከዚህም ቀደም ቬተራን (የአንጋፋነት) ፒን የሚባል ሽልማት የተሸለመ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ" የሚናገሩት አቶ ዱቤ ለአመታት የአትሌቶች ተወካይና ቴክኒካል ዳይሬክተር ሆነው ማገልገላቸው ለዚህ እንዳበቃቸው ገልፀዋል።

ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ጆን ሪድጌዎን የተላከላቸው ደብዳቤም 'ለረዥም ጊዜ ለሽልማት የሚገባ ስራ በአትሌቲክሱ ስለሰሩ ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል' የሚል ነው።

አቶ ስለሺ ብስራት በበኩላቸው "የተሸለሙት ፈጣን የሆነ ኮሚዩኒኬሽን ስላላቸው ነው" ብለዋል።

"በጥሩ ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያ የተመረጠች ሲሆን" ይህንን ደግሞ የሚመሩት አቶ ዱቤ ጅሎ መሆናቸውን አቶ ስለሺ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሁለቱም ኃላፊዎች ሽልማቱ ትልቅ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ዱቤ በአሁኑ ወቅት በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ የአትሌቲክስ ጥናት ውድድርና የአትሌቲክስ ልማት ይመራሉ።


አቶ ዱቤ ጅሎ ማናቸው?

  • የፌደራል ማረሚያ ቤት ለ18 አመታት ሯጭ ነበሩ
  • በአስር ሺ ሜትር፣ አገር አቋራጭና ማራቶን ተወዳድረዋል
  • በተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ላይ ቢያሸንፉም በኦሎምፒክ ውድድር ላይ ተሳትፈው አያውቁም
  • የአትሌቶች ተወካይ በመሆን ለረዥም ጊዜ አገልግለዋል
  • በሳቸው ጊዜ ታዋቂ አትሌቶች እንደነ ደራርቱ ቱሉ፣ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ ወርቁ ቢቂላ፣ ሐብቴ ጂፋር ነበሩ
  • በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር 2000 ዓ.ም የፌዴሬሽኑ ቴክኒካል ዳይሬክተር ሆኑ
  • በመካከል ለተወሰኑ ወራት አቋርጠው የነበረ ሲሆን' ኃይሌ ገብረሥላሴ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ወደ ቀድሞው ቦታቸው መልሷቸዋል።

ተያያዥ ርዕሶች