ትራምፕ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ለሳዑዲ የጦር መሳሪያ ሊሸጡ ነው

ትራምፕ ከሳዑዲው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን ጋር Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ማርች 2018 ላይ ትራምፕ ለሳዑዲው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን አሜሪካ ለሳዑዲ አረቢያ ለሽያጭ ያቀረበቻቸውን የጦር መሳሪያ አይነቶች በሰንጠረዥ ሲያሳዩ

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ለሳዑዲ አረቢያ እና ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች 8.1 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሣሪያ ሽያጭን አጸደቁ።

ሴኔቱ እና የተወካዮች ምክር ቤት የጦር መሣሪያዎቹ እንዳይሸጡ እገዳ ጥሎ ነበር።

ፕሬዝደንት ትራምፕ የሴኔቱ እና የምክር ቤቱ ውሳኔ "አሜሪካ በዓለም ላይ ያላትን ተፎካካሪነት ይቀንሳል፤ ከወዳጅ አገራት ጋር ያላትን ግነኙነትም ያሻክራል" ብለዋል።

አንዳንድ የኮንግረስ አባላት የጦር መሣሪያዎቹ በየመን ንጹሃን ዜጎች ላይ ጉዳት ያስከትላሉ ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

አባላቱ ሳዑዲ አረቢያ በየመን በሚደረገው ጦርነት ባላት ተሳትፎና በጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ግድያ አጥብቀው ኮንነዋል።

ስለ ጀማል ኻሾግጂ አሟሟት እስካሁን የምናውቃቸው እውነታዎች

ከኢንጅነር ስመኘው ሞት በኋላ ህዳሴ ግድብ ምን ላይ ደረሰ?

የሪፐብሊካኑ መሪ ሚች ማኮኔል ትናንት አመሻሽ ላይ ሴኔቱ፤ ትራምፕ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ውድቅ ያደረጉትን ውሳኔ መልሶ ለመሻር በቀጣይ ቀናት ድምጽ ሊሰጥ ይችላል ብለዋል።

ሚች ማኮኔል ይህን ይበሉ እንጂ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፤ ትራምፕ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ውድቅ ያደረጉትን ውሳኔ መልሶ ለመሻር በሴኔቱ ሁለት ሦስተኛ ድምጽ መኖር አለበት። ተንታኞች የትራምፕን ውሳኔ ውድቅ ለማድረግ ይህን አብላጫ ድምጽ በሴኔቱ ማግኘት የማይታሰብ ነው እያሉ ነው።

ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ሲጠቀሙ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ