አሜሪካ ከ16 ዓመት በኋላ የሞት ቅጣት ልትጀምር በመሆኑ ትችት ቀረበባት

የሞት ቅጣት የሚፈፀምበት አልጋ Image copyright Getty Images

አሜሪካ የሞት ቅጣትን ከ16 ዓመት በኋላ ልትጀምር መሆኑ ከዲሞክራቶችና ከመብት ተሟጋቾች ተቃውሞ ገጥሞታል።

በርካታ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የሚወዳደሩ ዲሞክራቶች የሞት ቅጣት እንዲቀር ጥሪ አቅርበዋል።

ሐሙስ እለት ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ ዊሊያም ባር፣ አምስት እስረኞች የሞት ቅጣት እንደሚፈፀምባቸው ተናግረው ነበር።

ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ የሞት ቅጣቱ የሚፈፀምባቸው ሰዎች በግድያ ወይንም ሕጻናትና እና አዛውንቶችን በመድፈር ተከስሰው የተፈረደባቸው እንደሆኑ ጨምረው ገልጸዋል።

ትራምፕ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ለሳዑዲ የጦር መሳሪያ ሊሸጡ ነው

ደኢሕዴን የሐዋሳና የሲዳማ ዞን አመራሮችን አገደ

ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው

ቅጣቱ የሚፈፀመው በመጪው ሕዳርና ታሕሳስ ወር እንደሆነም ቀን ተቆርጦለታል።

አቃቤ ሕጉ በመግለጫቸው "በሁለቱም ፓርቲዎች አስተዳደር የፍትህ ቢሮው በከባድ ወንጀል ተይዘው የተፈረደባቸው ግለሰቦች ላይ የሞት ቅጣት እንዲፈፀም ይፈልግ ነበር " በማለት "የፍትህ ቢሮው የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የተበዳዮችና ቤተሰቦቻቸው ኃላፊነት ስላለበት፣ በፍትህ ሥርአታችን ውስጥ የተቀመጠው ይህ ቅጣት ተፈፃሚ እንዲሆን እንጠይቃለን" ብለዋል።

የአቃቤ ሕጉ መግለጫ ይፋዊ ባልሆነ መልኩ እንዲቆም ተደርጎ የነበረው የሞት ቅጣት እንደገና ሊጀመር መሆኑን ያረጋገጠ ነው።

አሜሪካ ለመጨረሻ ጊዜ በሞት የቀጣችው ወንጀለኛ የ53 ዓመቱን ሉዊስ ጆንሰን ሲሆን፤ ግለሰቡ የገልፍ ጦርነት ወታደር አባል ነበር። ሉዊስ ጆንሰን የ19 ዓመቱን ወታደር ትራሲ ጆይ ማክብራይድን በመግደሉ ነበር የሞት ቅጣት የተበየነበት።

ይህ የሞት ቅጣት የተፈፀመው በ2003 ቀጥታ ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት ውሳኔ መሆኑ ይታወሳል።

በአሜሪካ 29 ግዛቶች የሞት ቅጣት ሕጋዊ ነው። እኤአ ከ1976 ጀምሮ በሞት በመቅጣት ከፍተኛውን ቁጥር የያዘችው ግዛት ቴክሳስ ስትሆን 561 ወንጀለኞችን በሞት ቀጥታለች።

ቨርጂኒያ 113 ወንጀለኞችን፣ ኦክሎሀማ ደግሞ 112 በመቅጣት ይከተላሉ።

በአሜሪካ በአሁኑ ሰዓት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ቀናቸውን የሚጠባበቁ 2673 እስረኞች ይገኛሉ። ካሊፎርኒያ 733 የሞት ፍርደኞች ሲኖሯት፤ ከ1976 ጀምሮ 13 የሞት ቅጣቶችን ብቻ አስፈፅማለች።