ብጉርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

ብጉር ለምን ይከሰታል? Image copyright Getty Images

በዓለማችን ከሚገኙ ዕድሜያቸው 11-30 ዓመት የሆናቸው ሰዎች መካከል 80 በመቶ የሚያህሉ ቢያንስ አንዴ በሰውነት ክፍላቸው ላይ ብጉር ይወጣባቸዋል።

ብጉር በዘር ሊተላለፍ የሚችል የቆዳ ችግር ነው። አብዛኛውን ጊዜ ብጉር ፊት ላይ እንዲወጣ የሚያደርገው ቅባት መሳይ ነገር የሚያመነጭ እጢ እና ከቆዳ ስር የሚገኝ ባክቴሪያ መሆኑን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቆዳ እና የአባላዘር በሽታ ትምህርት ክፍል መምህር እና ሃኪም የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ዳኛቸው ሺበሺ ናቸው።

በዕጢ አማካኝነት የሚመነጨው ይህ ቅባት መሳይ ፈሳሽ በቆዳችን ላይ ቀዳዳ በመፍጠር ከቆዳ ሥር ወደ ሚገኘው ባክቴሪያ በመግባት ብጉር እንዲፈጠር ያደርጋል።

ሞባይል ለኢትዮጵያ እናቶችና ህፃናት ጤና

የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች፤ በተለይም ደግሞ ቅባታማ ምግቦች ፊት ላይ ለሚወጣ ብጉር ምክንያት ናቸው ተብሎ የሚታመነው ስህተት መሆኑን ዶ/ር ዳኛቸው ይናገራሉ። ከቢቢሲ ኧርዝ ላብ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው ከሆነ ደግሞ ቅባታማ ይዘት ካላቸው ምግቦች ይልቅ ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸው ምግቦች እና መጠጦች በፊት ላይ ብጉር እንዲወጣ ያደርጋሉ።

ለምሳሌ ለውዝ ከመብላት ይልቅ የለስላሳ መጠጦችን መጠቀም ለብጉር ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጋል።

ዶ/ር ዳኛቸው "ብጉር በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ከሚኖሩ ሰዎች ይልቅ ብዙውን ጊዜ የተሻለ ህይወት በሚመሩ ሰዎች ላይ ይከሰታል። የወር አበባ ሊመጣ ሲል ብጉርም ፊት ላይ ሊወጣ ይችላል" ይላሉ።

ብጉር ብዙውን ጊዜ በታዳጊዎች እና ወጣቶች ላይ ይስተዋል አንጂ በአዋቂዎች ላይም ይወጣል።

ፊታቸው ላይ ብጉር መውጣቱ የሚያስጨንቃቸው ወጣቶች የህክምና እርዳታ ፍለጋ ወደ ሆስፒታሎች እንደሚመጣጡ ዶ/ር ዳኛቸው ይናገራሉ። ህክምናውም ከሶስት እስከ ስድስት ወራት ሊፈጅ እንደሚችል የሚያስረዱት ዶ/ር ዳኛቸው፤ ብጉር ፊት ላይ የሚጥለውን ምልክት ማስወገድ ግን ቀላል እንደማይሆን ይናገራሉ።

ጤና የራቀው የፈለገ ህይወት ሆስፒታል

ብጉርን መከላከል ይቻላል?

ብጉር እንዳይወጣ ማድረግ አይቻልም። ብጉር ከወጣ በኋላ ግን በእጅ ለማፍረጥ መሞከሩ በፊታችን ላይ አላስፈላጊ ምልክቶችን ጥሎ እንዲያልፍ የሚያደርግ ስለሆነ ከዚህ መሰሉ ተግባር መቆጠብ እንደሚገባ ዶ/ር ዳኛቸው ይናገራሉ።

ዶ/ር ዳኛቸው እንደሚሉት በጸሃይ ጨረር ምክንያት ብጉር የሚወጣባቸው ሰዎች አሉ። እንደዚህ አይነት ሰዎች በተቻላቸው መጠን የጸሃይ ጨረር መካላከያ ክሬሞችን በመጠቀም ብጉር መከላከል ይችላሉ ይላሉ።

የቢቢሲ ኧርዝ ላብ መረጃ እንደሚያመላክተው ደግሞ የስኳር መጠናቸው ከፍተና የሆኑ መግቦችን እና መጠጦችን ማቆም፣ በሶስት ወር እንዴ 30ሚሊ ግራም የዚንክ እንክብል መውሰድ ብጉር ሊከሰት የሚችልበትን አጋጣሚ በ15 በመቶ እንደሚቀንስ ያትታል። መረጃው በተጨማሪም ፊትን አብዝቶ አለመኳኳል፣ ጽጉር እና ሙሉ ሰውነትን ዘወትር መታጠብ ብጉር እንዳይከሰት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።

በየቀኑ አንድ ሚሊየን ሰው በአባላዘር በሽታ ይያዛል

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ