የዱባዩ መሪና ጥላቸው የኮበለለችው ባለቤታቸው ወደ ፍርድ ቤት ሊያመሩ ነው

ልዕልት ሀያ ቢንት አል-ሁሴን የዱባይ መሪ ከሆነው ባለቤቷ ሞሀመድ አል ማክቱም ጋር Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ልዕልት ሀያ ቢንት አል-ሁሴን የዱባይ መሪ ከሆነው ባለቤቷ ሞሀመድ አል ማክቱም ጋር

በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ስማቸው ከፍ ተደርጎ ከሚጠሩት አለቆች መካከል እንዱ የሆኑት የዱባይ ገዥ ጥላቸው ወደ ለንደን ከኮበለለችው ባለቤታቸው ጋር ስለ ልጆቻቸው አስተዳደግ እጣ ፈንታ ውሳኔ ለማግኘት ወደ ፍርድ ቤት ሊያመሩ እንደሆነ ተነገረ።

ልዕልት ሀያ ቢንት አል-ሁሴን የዱባይ መሪ ከሆነው ባለቤቷ ሞሀመድ አል ማክቱም ሸሽታ እንግሊዝ፣ ለንደን ውስጥ ከተደበቀች ሳምንታት አልፈዋል። ባለቤቷን ጥላ መኮብለሏን ተከትሎ ሕይወቷ አደጋ ውስጥ መሆኑንም ተናግራለች።

የዱባይ ልዕልት ከባለቤቷ ሸሽታ ለንደን ተደብቃለች

የተተከሉት ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ?

ብሔራዊ አገልግሎት መንፈሳዊ ህይወቱን የነጠቀው ኤርትራዊው ዲያቆን

የ69 ዓመቱ ቢልየነር ሼህ ሞሀመድ አል ማክቱም ባለቤታቸው ጥላቸው በመኮብለሏ ብስጭታቸውን ገልጸዋል።

ልዕልት ሀያ ቢንት አል-ሁሴን ከሼህ ሞሀመድ አል ማክቱም ስተሸሽ ሦስተኛ የቤተሰብ አባል ያደርጋታል።

ወደ ፍርድ ቤት የሚሄደው ጉዳይ ልዕልቷ ከባለቤቷ ስትሸሽ ይዛቸው ስለሄደቻቸው ልጆቻቸው ነው ተብሏል።

በጆርዳን የተወለደችው ልዕልት ሀያ፤ በአሁኑ ወቅት ጆርዳንን እያስተዳደሩት ያሉት ንግሥት አብዲላሂ ሁለተኛ ወንድሟ ናቸው። ልዕልት ሀያ ትምህርቷን የተከታተለችው እንግሊዝ በሚገኙ ቅንጡ የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሲሆን፤ ልዕልቷ በኦሎምፒክ በፈረስ ግልቢያ ውድድር ተሳታፊም ነበረች።

እአአ 2004 ከሼህ ሞሀመድ ጋር ትዳር የመሰረተችው ልዕልቷ፤ የሼሁ ስድስተኛ ባለቤት ሆና ነበር። የ70 ዓመቱ ሼህ ሞሀመድ ከተለያዩ ሚስቶች 23 ልጆች እንደወለዱ ይነገራል።

የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የተከታተለችው ልዕልት እስከወዲያኛው እንግሊዝ መቆየት ትፈልጋለች። ይሁን እንጂ ባለቤቷ ወደ ዱባይ እንድትመለስ የሚጠይቅ ከሆነ፤ የዱባይን እና የለንደንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ጥያቄው ለዩናይት ኪንግደም መንግሥት ከፍተኛ እራስ ምታት እንደሚሆን ዲፕሎማቶች ይናገራሉ።

የ70 ዓመቱ ቢልየነር ሼህ ሞሀመድ አል ማክቱም ባለቤታቸው ጥላቸው ከኮበለለች በኋላ በኢንስታግራም ገጻቸው በቁጣ የተሞላ ግጥም አስፍረዋል። ግጥሙን ለማን እንደጻፈፉ ባይናገሩም አንዲት ሴትን "ከዳተኛ" ብለው ገልጸዋል።

ልዕልቷ ለምን ኮበለለች?

ለልዕቷ የቀረቡ ምንጮች እንሚሉት፤ ልዕልቷ ለመኮብለል የወሰነችው ከሼህ ሞሀመድ ልጆች አንዷ ስለሆነችው ላቲፋ ቢን ሞሃመድ አልማክቱም አስደንጋጭ መረጃ በማግኘቷ ነው።

የሼሁ ልጅ ከአንድ ዓመት በፊት ከዱባይ ኮብልላ ነበር። በአንድ የፈረንሳይ ዜጋ በሆነ የቀድሞ ሰላይ ድጋፍ ባህር ተሻግራ ከዱባይ ከሸሸች በኋላ በሕንድ ጠረፍ አካባቢ በሼሁ ወታደሮች ተይዛ ወደ ዱባይ እንድትመለስ ተደርጓል።

ከዱባይ ለመሸሽ ሙከራ ከማድረጓ በፊት በተቀረጸ ቪዲዮ ላፊፋ፤ "ሞቻለሁ ወይም እጅግ ከባድ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እገኛለሁ" ስትል የወደፊት እጣ ፈንታዋ ከባድ መሆኑን ጠቁማ ነበር። በወቅቱ ልዕልት ሀያና ላቲፋ ቢንት ሞሃመድ አል ማክቱም በዱባይ ደህንነቷ ተጠብቆ ትገኛለች ብላ ነበር።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላቲፋ ከሕንድ ባህር ዳርቻ ላይ በወታደሮች ያለ ፍቃዷ ታፍና ነው የተወሰደችው በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ይሁን እንጂ ልዕልቷ ዘግይቶ ስለ ላቲፍ አዲስ መረጃዎች ስለደረሷት እንዲሁም ከባለቤቷ ዘመዶች የሚደርስባትን ጫና ምክንያት በማድረግ ከባለቤቷ ሸሽታለች ተብሏል።