የታዋቂዋ ወጣት አስክሬን ሻንጣ ውስጥ ተገኘ

ኤካቴሪና ከሞስኮ የህክምና ትምህርት ቤት በቆዳ ህክምና የዶክትሬት ዲግሪዋን ተቀብላ ነበር። Image copyright katti_loves_life/Instagram
አጭር የምስል መግለጫ ኤካቴሪና ከሞስኮ የህክምና ትምህርት ቤት በቆዳ ህክምና የዶክትሬት ዲግሪዋን ተቀብላ ነበር።

ተጽእኖ ፈጣሪዋ እና ኢንስታግራም ላይ ብዙ ተከታዮች ያሏት ሩሲያዊት፤ ሞስኮ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ አስክሬኗ ሻንጣ ውስጥ ተገኝቷል።

ፖሊስ እንዳለው የ24 ዓመቷ ወጣት ኤካቴሪና ካራግላኖቫ በስለት ተወግታ ስለመሞቷ በአስክሬኑ ላይ ምልክቶች ታይተዋል።

በኢንስታግራም ላይ ከ85ሺህ በላይ ተከታዮች የነበሯት ኤካቴሪና በቅርቡ በህክምና ዘርፍ የዶክትሬት ድግሪዋንም ተቀብላ ነበር።

ጠብ አጫሪና ጥቃት አድራሽ የፌስቡክ ፖስቶችን እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል?

ኤካቴሪና ከቤተሰቧቿ ጋር ግንኙነት አለማድረጓን ተከትሎ በቤተሰብ አባላት ላይ ጥርጣሬ ካደረ በኋላ ነው አስክሬኗ ሊገኝ የቻለው።

የገዳዩ ማንነት እስካሁን ባይታወቅም የተገደለችው ግን በቅናት መንፈስ በተነሳሳ ሰው ሳይሆን አይቀርም ሲል ፖሊስ ቅድመ ግምቱን አስቀምጧል።

ሞስኮበስኪይ ኮመሶሞሌትስ የተሰኘ የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው ከሆነ ኤካቴሪና ከዚህ ቀደም የነበራትን የፍቅር ግንኙነት በማቋረጥ አዲስ ፍቅር መጀመሯን እና ልደቷን ለማክበር ወደ ሆላንድ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ ነበረች።

ኤካቴሪናን ለቀናት ያላገኙት ወላጆች ተከራይታ ወደ ምትኖርበት የጋራ መኖሪያ ቤት ያቀናሉ። ተከራይታ ከምትኖርበት ቤት ከደረሱም በኋላ ከአከራይዋ ቁልፍ በመቀበል ወደ ውስጥ ሲዘልቁ አስክሬኗን ሻንጣ ውስጥ ተከቶ አግኝተዋል።

ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ ሰባት ምልክቶች

ድንጋጤ ውስጥ የነበሩት ወላጆች የአምቡላንስ እርዳታን ቢጠይቁም የልጃቸው ህይወት ቀድሞ ማለፉ ከጤና ባለሙያዎች ተነግሯቸዋል ሲል የሩሲያው መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

ኤካቴሪና አንገቷ ላይ በስለት ስለመቆረጧ ምልክት መኖሩም ተዘግቧል።

ከጥቂት ወራት በፊት ከዚህ በታች የተመለከተው በኢንስታግራም ገጿ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት፤ መኖሪያ ቤቷን እንዴት እንደምታስጌጥ እና ስላሰበቻቸው የውጪ አገር የጉዞ እቅዶች ብዙ ብላ ነበር።

ፖሊስ ወንጀሉ የተፈጸመበት መሳሪያ በቦታው አለማግኘቱን የተናገረ ሲሆን፤ የቀድሞ እጮኛዋ በጠፋችበት ቀን ወደ ቤቷ ሲገባ በሲሲቲቪ ካሜራ መታየቱን ፖሊስ አሳውቋል።

"የአደገኛ ግለሰቦች" የፌስቡክ ገጽ መዘጋት ጀመረ

ፖሊስ ይህን ይበል እንጂ የቀድሞ ፍቅረኛዋ ከግድያው ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር ስለመዋሉ ያለው ነገር የለም።

ኤካቴሪና በኢንስታግራም ገጿ ላይ የምትለጥፋቸው ፎቶግራፎች ከትውልድ ሃገሯ ሩሲያ ተነስታ ወደ በርካታ የዓለማችን ከፍሎች መጓዟን ያሳያሉ።

ለመጨረሻ ግዜ የለጠፈችው በግሪክ ሃገር ኮርፉ በተሰኘ ደሴት ላይ የተነሳችው ፎቶግራፍ ሲሆን "ጉዞ ማድረግ እወዳለሁ። በየትኛው ሃገር ግን ከ3-5 ቀናት በላይ መቆየት አያስደስተኝም" የሚል ጽሁፍን አብራ አያይዛለች።

ከኢንስታግራም ተከታዮቿ በተጨማሪ ኤካቴሪና በሺዎች የሚቆጠሩ የሚጎበኙት ስኬታማ የሆነ የጉዞ ማስታወሻ መጣጥፎቿን የምታስነብብበት ድረ-ገጽም ነበራት።

ከዚህ በተጨማሪም ኤካቴሪና ከሞስኮ የህክምና ትምህርት ቤት በቆዳ ህክምና የዶክትሬት ዲግሪዋን ተቀብላ ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች