የሳምሰንግ ትርፍ ከ50 በመቶ በላይ አሽቆለቆለ

ሳምሰንግ ካምፓኒ Image copyright Getty Images

የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች አምራቹ ሳምሰንግ በሁለተኛው ሩብ ዓመት የምርቱ ትርፋማነት እንዳሽቆለቆለበትና ይህም ወደፊት ተግዳሮቶች ሊያጋጥሙት እንደሚችል ማስጠንቀቂያ እንደሆነ አስታወቀ።

የአዲሱ ሳምሰንግ ጋላክሲ S9 በካሜራ ብቃት ላይ አተኩሯል

ሳምሰንግ እንደ መጽሐፍ የሚገለጥ ስልክ አመረተ

የዓለማችን ትልቁ ዘመናዊ ስልኮችንና የኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን አምራቹ ኩባንያ- ሳምሰንግ እንዳለው ትርፋማነቱ ከዚህ ዓመት ቀድሞ ባለው የበጀት ዓመት በ56 በመቶ ቀንሷል።

ለዚህም በአሜሪካና በቻይና መካከል እየተካሄደ ያለው የንግድ ጦርነት ምክንያት ነው ተብሏል።

ይህም ብቻ ሳይሆን አምራች ድርጅቱ በሶልና ቶክዮ ባለው የንግድ ወረፋ ምክንያት ችግር እያጋጠመው እንደሆነ ገልጿል።

በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ድርጅቱ እስከ ሰኔ ወር ባሉት ሦስት ወራት የሥራ ማስኬጃን በመቀነስ ከሚገኝ ትርፍ 6.6 የኮሪያ ዋን (5.6 ቢሊየን ዶላር)፤ ባለፈው ዓመት ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ትርፉ 14.87 የኮሪያ ዋን (12.6 ቢሊየን ዶላር) ጋር ሲነፃፀር፤ 56 በመቶ መቀነሱን አስታውቋል።

ሳምሰንግ ባወጣው መግለጫ እንዳለው በፍላጎት ደረጃ ትንሽ መሻሻሎች ቢታይም በምርቶቹ ላይ የገበያ ማጣትና የዋጋ ቅናሽ ግን ታይቷል።

"ኩባንያው እያጋጠመው ያለው ተግዳሮት በንግዱ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚክ ሁኔታ መለዋወጥም ተፈታትኖታል" ብሏል በመግለጫው።

ጃፓን በቅርቡ ወደ ውጭ የሚላኩ የኢንዱስትሪ ቁሳቁሶች፤ 'ሴሚ ኮንዳክተርስ' እና 'ስክሪኖች' ለመስራት የሚውሉ ምርቶች ላይ ቁጥጥር ማድረግ ጀምራለች።

ይህ እንቅስቃሴም ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጅ እቃዎች አቅርቦት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል በሚል አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል። በመሆኑም የሳምሰንግን የወደፊት የምርት አቅርቦት ሊፈታተነው እንደሚችል ተጠቁሟል።

ኩባንያው በቅርቡ እንዳስተዋወቀው ተጣጣፊ ስልኩ፤ አዳዲስ ምርቶች ማስተዋወቅ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ እና በሦስተኛው ሩብ ዓመት ላይ ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ታጣፊው የሳምሰንግ ስልክ የ'ስክሪን' መሰበር ወቀሳ ቀረበበት

ሳምሰንግ በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ አዲሱን ተጣጣፊ ስልኩ የስክሪን መሰበር ወቀሳ ካጋጠመው በኋላ ለገበያ ለማቅረብ እንደዘገየም አስታውሰዋል።

በአዲሱ ስልኩ ላይ ያጋጠመው ችግር በድርጅቱ ላይ አመኔታን ያሳጣ ሲሆን ይህም የዘመናዊ ስልኮች ሽያጭ ለመቀነሱና ከቻይናው ሁዋዌ ጋር ካለው የንግድ ውድድር ላይ መጥፎ አሻራ እንዳሳረፈ ተገልጿል።

ሳምሰንግ ተጣጣፊው ጋላክሲ ስልኩ ተሻሽሎ በመጭው መስከረም ወር ለገበያ እንደሚቀርብ ያስታወቀው ባለፈው ሳምንት ነበር።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ