ሰሜን ኮሪያ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ ሁለት ጊዜ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች

ሰሜን ኮሪያ ሁለት ባለስቲክ ሚሳዔሎችን ተኩሳለች Image copyright AFP

ሰሜን ኮሪያ አጭር ርቀት ተጓዥ ሁለት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን በምስራቃዊ ወደቧ በኩል ማስወንጨፏን ደቡብ ኮሪያ አሳውቃለች፤ ሙከራው በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተደረገ ነው።

ሁለቱ ባለስቲክ ሚሳዔሎች ዎንሳን ከተባለው አካባቢ ረቡዕ ንጋት 11 ሰዓት ገደማ ላይ ነው የተተኮሱት።

ወርሃ ሰኔ ላይ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከተገናኙ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያው የሚሳዔል ሙከራ ነው ተብሏል።

ሰሜን ኮሪያ፤ ሙከራው ከአሜሪካ ጋር ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እየሞከረች ያለችውን ደቡብ ኮሪያ ለማስበረገግ ነው ብላለች።

ሰሜን ኮሪያ ከኦሎምፒክ ቀደም ብሎ የጦር ትዕይንት አካሄደች

ሚሳዔሎቹ 250 ኪሎ ሜትር ርቀት የመጓዝ አቅም ያላቸው፤ ወደላይ ደግሞ እስከ 30 ኪሎሜትር ድረስ መምዘግዘግ የሚችሉ ናቸው። ማረፊያቸውን ደግሞ የጃፓን ውቅያኖስ ተብሎ የሚጠራው ሥፍራ ላይ አድርገዋል።

የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስትር ጄዎንግ ኬዮንግ-ዱ ሚሳኤሎቹ ከዚህ በፊት ታይተው የማይታወቁና በይዘታቸው ለየት ያሉ ናቸው ብለዋል።

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ የሚሳኤል ሙከራው በጃፓን ላይ ያደረሰው አንዳችም ጉዳት የለም ሲሉ ተደምጠዋል።

ሰሜን ኮሪያ በ37 ዓመት ያልታየ ድርቅ አጋጠማት

ሰሜን ኮሪያ ይህንን ሙከራ ከማድረጓ ስድስት ቀናት አስቀድሞ እያንዳንዳቸው 690 እና 430 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችሉ ሚሳኤሎችን አስወንጭፋ ነበር።

ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ በየዓመቱ ወታደራዊ ልምምድ ያካሂዳሉ፤ ይህ ደግሞ ሰሜን ኮሪያን የሚያስደስት ጉዳይ አይደለም። የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል ማስወንጨፍ ደቡብ ኮሪያ እንድትበረግግ፤ አሜሪካም እንድትደንግጥ ለማድረግ እና ይህን ልምምድ እንዳታካሂድ ለማድረግ ነው ተብሏል።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ሰሜን ኮሪያ ለምን ኑክሊዬርን መረጠች?

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ