ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመለየት 'አይጥ' ጥሩ አድማጭ ሳትሆን አትቀርም ተባለ

የሰው ልጅ ጆሮ ሊስተው የሚችለውን ድምፅ አይጦች ሊሰሙት እንደሚችሉ ተመራማሪዎች ተስፋ ሰንቀዋል Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የሰው ልጅ ጆሮ ሊስተው የሚችለውንና ያልተለመደ ድምፅ አይጦች ሊሰሙት ይችላሉ ሲሉ ተመራማሪዎች ተስፋ ሰንቀዋል

ሀሰተኛ መረጃን ለመዋጋት አዲስ መሳሪያ ሊኖር ይችላል ተብሏል - አይጥ።

ሀሰተኛ መረጃዎች እየተፈበረኩ ባለበት ጦር ሜዳ ጥልቅ የሆኑ ሀሰተኛ ተንቀሳቃሽ ምስልንና የድምፅን ስሪት ለመለየት፣ ለማየትና ለመስማት ተመራማሪዎች ፊታቸውን ወደ አዲስ ምርምር አዙረዋል።

ይህ ሃሳብ በመጀመሪያ የተሞከረው በኦሪጎን የኒሮሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ነው። የጥናት ቡድኑ አይጥ ያልተለመዱ ንግግሮችን እንዲለዩ ለማሰልጠን እየሰሩ ይገኛሉ።

ፌስቡክ አፍሪካ ላይ የተቃጡ ገጾችን ዘጋ

ትራምፕ መማገጣቸውን ያድበሰበሱበት የድምጽ መረጃ ይፋ ወጣ

ጥናቱ ፌስቡክና ዩቲዩብ ሐሰተኛ መረጃዎቹ በኢንተርኔት አማካይነት ከመዛመታቸው በፊት ለመፈተሽ እንደሚያግዛቸው ተስፋ የተጣለበት ነው። ታዲያ እነዚህ ድርጅቶች የራሳቸው አይጥ እንዲኖራቸው አይጠበቅባቸውም።

"ሀሰተኛ መረጃን ዩቲዩብ ላይ የሚመረምሩ አይጦች በክፍሉ ውስጥ ተሰማርተው ማሰብ በጣም ደስ ይላል " የሚሉት የፕሮጀክቱ ተመራማሪ ጆናታን ሳውንደርስ ምርምሩ በተለያየ ምክንያት ተግባራዊ ይሆናል ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል። "ዋናው የምርምሩ ዓላማ ትምህርት ለመውሰድና ከዚያም በኮምፒዩተር ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ነው" ሲሉ በመግለፅ።

የፕሮጀክቱ ኃላፊ ሳንደርስ እና የጥናት ቡድኑ በበኩላቸው አንድን ድምፅ ከሌላው ወይም አንድን ቃል ከሌላው የሚለዩ የራሳቸውን አይጥ ማሰልጠናቸውን ተናግረዋል።

በሃሰተኛ ዜናዎች "የሞቱ" የኪነጥበብ ሰዎች

"'ቡህ ' እና 'ጉህ' የሚሉ ድምፆችን በተለያየ የቃላት አገባብ፣ በተለያዩ አናባቢዎች የተከበቡ ' ቦይ ፣ ቢህ፣ ባህ' እንዲለዩ አይጧን አሰልጥነናል፤ የተወሳሰበ የንግግር ድምፆችን መረዳት ይችላሉ፤ በመሆኑም ትክክለኛውን ትክክለኛ ካልሆነው ንግግር መለየት እንደሚችሉ አሰብን " ይላሉ።

በዚህም ምክንያት ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመለየት እነርሱን ማሰልጠን እንደሚቻል ማሰባቸውን ይናገራሉ።

አይጦቹ 80 በመቶ በሚሆነው ጊዜ ትክክለኛውን ድምፅ መለየት ሲችሉ ሽልማት ይበረከትላቸው ነበር።

ምንም እንኳን ምላሻቸው ሙሉ በሙሉ ትክክል ባይሆንም ጥልቅ የሆኑ ሀሰተኛ ንግግሮችን ለመለየት ጠቃሚ ግብዓት መስጠት ይችሉ ነበር ብለዋል።

እነዚህን ሀሰተኛ መረጃዎች መርማሪዎችን ለማሰልጠን ከ100 እስከ 500 ዶላር እንደሚወስድ ይገመታል" ሲሉ ባልቲሞር ላይ ተቀማጭነቱን ያዳረገው የሳይበር ደህንነት ድርጅት ባለሙያ ማቲው ፕራይስ ይናገራሉ።

ፕራይስ በንግግራቸው እንዳሉት አይጦቹ ያልተለመዱ የጭንቅላት እንቅስቃሴዎችን፣ ወጥነት የሌለው የብርሃን አጠቃቀምን ለመለየት ውጤታማ የሆነው ዘዴ መሆኑን በኮንፈረንሱ ላይ ተናግረዋል።

"ምን አልባት በ2020 ምርጫ በርካታ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲወጡ ላናይ እንችላለን " ሲሉም አክለዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ