የሆንግ ኮንግ ፖሊስ ሰልፈኛ አስመስሎ ፖሊስ ማሰማራቱን አምኗል

የሆንግ ኮንግ ፖሊስ፡ «ሰልፈኛ አስመስን ፖሊስ አሰማርተናል» Image copyright Reuters

የሆንግ ኮንግ ፖሊስ እሁድ ዕለት በከተማዋ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተሳታፊ በማስመሰል የፖሊስ መኮንኖችን ማሰማራቱን አምኗል።

የፖሊስ አፈ-ቀላጤ የሆኑት ኃላፊ 'አዎ አሰማርተናል' ሲሉ አምነው 'ይህንን ያደረግነው አመፀኞችን ለመበታተን ነው' የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የሆንግ ኮንጉን ተቃውሞ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከፖሊሶች ጋር በመተባበር ሰልፈኞችን ሲያስሩ ከታዬ በኋላ ነው ነገሩ የከረረው። ተቃዋሚዎቹ ጉዳዩን ይጣራልን ሲሉ አቤት ብለዋል።

ተቃውሞ በቻይና፡ መንግሥት 'የውጭ ኃይሎችን' እየወቀሰ ነው

ቻይና ወንጀል ፈፅመው ወደ ሆንግ ኮንግ የሚያመሩ ሰዎችን የሆንግ ኮንግ አስተዳደር አሳልፎ እንዲሰጣት የሚያዝ ሕግ ለማውጣት ማቀዷን ተከትሎ ነው የሆንግ ኮንግ ነዋሪዎች አደባባይ የከተሙት።

ይኸው ከሁለት ወራት በኋላም ሆንግ ኮንግ በሕዝባዊ ተቃውሞ እና እሥር በመናጥ ላይ ትገኛለች። ሰኞ ዕለት ሰልፈኞች የሆንግ ኮንግ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን በቁጥጥር ሥር በማዋላቸው ምክንያት በረራዎች እንዲሠረዙ ሆነዋል።

ምንም እንኳ የሃገሪቱ ባለሥልጣናት አውሮፕላን ማረፊያው ሥራ ጀምሯል ቢሉም በርካታ አየር መንገዶች አሁን በረራቸውን እንደሠረዙ ናቸው።

የሆንግ ኮንግ የሕዝብ እንደራሴዎች ተቧቀሱ

የፖሊስ አፈ-ቀላጤ እና ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት ታንግ ፒንግ-ኩዌንግ 'ባንዳ ፖሊሶች' ማሰማራታቸውን ደግፈው ተከራክረዋል።

«እኛ ፖሊሶቻችን ሰልፍ ውስጥ ገብተው አመፅ እንዲቀሰቅሱ አይደለም ያሰማራናቸው፤ እጅግ አመፀኛ የሆኑ ሰልፈኞችን ለቅመው እንዲያመጡልን እንጂ።»

አንዲት ሴት ዓይኗ ግድም ተመታ ደም ሲፈሳት የሚያሳይ ፎቶ በማሕበራዊ ድር-አማባዎች መሰራጨቱን ተከትሎ ፖሊስ ወቀሳ እየዘነበበት ይገኛል። ፖሊስ 'ከደሙ ንፁህ ነኝ' ቢልም።

መቆሚያ ባላገኘው የሆንግ ኮንግ ሕዝባዊ ተቃውሞ የፖሊስ መኮንኖችን ጨምሮ በርካታ ሰልፈኞች መጎዳታቸው እየተዘገበ ነው።

የቻይና ሕግ የሆንግ ኮንግን ነፃነት የሚገዳደር ነው፤ አልፎም ቻይና የፖለቲካ ሰዎችን ማሠር ሲያሻት ልትጠቅመበት ያሰበችበት ሕግ ነው ሲሉ ተቃዋሚዎች ይተቻሉ።

ባህር አቋራጩ የቻይና ድልድይ ተከፈተ

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ