በሞዛምቢክ የውበት መጠበቂያ ምርቶች ፋብሪካ ሠራተኞች ራሳቸውን ሳቱ

በቻይና ፀጉር የማዘጋጀት ሂደት Image copyright GREG BAKER

በሞዛምቢክ የውበት መጠበቂያ ምርቶችን የሚያመርት ፋብሪካ ሠራተኞች በቂ አየር ባለማግኘታቸው ራሳቸውን እየሳቱ መሆኑ ተገለፀ።

ባለፈው ዓመት ሕዳር ወር 132 የሚሆኑ የፋብሪካው ሠራተኞች ለሕመም ተዳርገው ሕክምና ተከታትለዋል።

ታዋቂው ኩባንያ ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞችን ''ይበድላል'' ተባለ

ፕሬዚዳንቱ የቁንጅና አሸናፊዋን በተፈጥሮ ፀጉሯ ልታጌጥ ይገባል ሲሉ ተቹ

ባሳለፍነው ሰኞም 72 ሠራተኞች ለተመሳሳይ ችግር ተዳርገው በማቶላ በሚገኘው ማፑቶ ሆስፒታል መላካቸው ተዘግቧል።

ሠራተኞቹ ሆስፒታል በገቡበት በዚያው ዕለት ከሆስፒታል የወጡ ሲሆን የሆስፒታሉ ዶክተሮች ግለሰቦቹ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደማይገኙ አስታውቀዋል።

የፋብሪካው አስተዳደር ሠራተኞቹ በተደጋጋሚ ለሕመም በመዳረጋቸውና በሌሎች ምክንያቶች ወቀሳ ደርሶበታል።

ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት የፋብሪካው በርና መስኮቶች ዝግ በመሆናቸው አየር እንደልብ አይዘዋወርም።

ለሽያጭ የሚያዘጋጅ 'የህፃናት ፋብሪካ' በናይጄሪያ

በብዛት ሰው ሰራሽ ፀጉርን የያዙ እና ሌሎች ጥሬ እቃዎች የተቀመጡባቸው ሳጥኖች በፋብሪካው ውስጥ ታጭቀው ይገኛሉ።

ይህም በቤቱ ውስጥ ጥቃቅን የሆኑ በካይ ቅንጣጢቶች በአየሩ ውስጥ እንደተጠራቀሙና ሠራተኞቹ እነዚህን በካይ ነገሮች ከሚስቡት አየር ጋር ለመማግ በመዳረጋቸው እንደሆነ ሪፖርቱ ተገልጿል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ