የሱዳን ሠራዊትና ተቃዋሚዎች ሥልጣን ለመጋራት ተስማሙ

ስምምነቱ ሲፈረም Image copyright EBU

የሱዳን ገዢ ወታደራዊ ምክር ቤት እና የተቃዋሚዎቹ ጥምረት ሥልጣን ለመጋራት የሚያስችላቸውን ወሳኝ ስምምነት ካርቱም ውስጥ ተፈራረሙ።

ስምምነቱ ወደ ምርጫና የሲቪል አስተዳደር ለሚደረገው ሽግግር የሚያገለግል ወታደራዊ መሪዎቹንና ሲቪሎችን ያካተተ አዲስ ምክር ቤት እንዲቋቋም የሚያስችል ነው።

በሱዳን ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው የሚነገርላቸው ኃያሉ ሰው ሞሃመድ "ሄሜቲ" ዳጎሎ የተፈረመው ስምምነት ላስቀመጣቸው ሃሳቦች እንደሚገዙ ቃል ገብተዋል።

በጭቆና ውስጥ ለሦስት አስርታት ያህል የቆዩ ሱዳናዊያን ዲሞክራሲያዊ ጥያቄን አንስተው ለተቃውሞ አደባባይ ለሳምንታት ከቆዩ በኋላ ነበር ለረጅም ጊዜ ሥልጣን ላይ የቆዩት ኦማር አል በሽር ከሥልጣናቸው የተወገዱት።

የኢትዮጵያን አደራዳሪነት የሱዳን ህዝብ እንዴት ይመለከተዋል?

በሱዳን የዳቦ ዋጋ በመጨመሩ ተቃወሞ ተቀስቅሷል

የኢትዮጵያውና የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትሮችና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ካርቱም ውስጥ በተደረገው የፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙ የአካባቢው ሃገራት መሪዎች ናቸው።

በተፈረመው ስምምነት መሰረት ስድስት ሲቪሎችና አምስት ጄነራሎችን ይዞ የሚመሰረተው ሉዓላዊው ምክር ቤት ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ሃገሪቱን የማስተዳደር ሥልጣን ይኖረዋል።

ከሦስት ዓመታት ትንሽ ዘለግ ላለ ጊዜ በሚቆየው የምክር ቤቱ ሥልጣን ዘመን ሁለቱ ወገኖች እየተፈራረቁ የመሪነት ሚናውን ለመወጣት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ተያያዥ ርዕሶች