ፀረ-መውለድ፦ ልጆች እንዳይወለዱ የሚቃወመው ፍልስፍና

ፀረ መውለድ

የሰው ልጅ መራባት የለበትም የሚል እምነት አላቸው። እነማን? መውለድን የሚቃወሙት የፀረ መውለድ ፍልስፍና ተከታዮች አላማቸውንስ ለማስፈፀም ምን ያህል ይጓዛሉ?

"መሬት ውስጥ አንድ ፍንዳታ ተፈጥሮ ሁሉንም ነገር ድምጥማጡ ቢጠፋ እንዴት ጥሩ ነበር"

በምስራቃዊዋ እንግሊዝ የሚኖረው የ29 አመቱ ቶማስ መሬትን የማፈንዳቱ ጉዳይ እንዲያው በሃሳብ ደረጃ የሚመላለስ ቢሆንም፤ በአንድ ጉዳይ ግን እርግጠኛ ነው፤ የሰው ልጅ ዘሩን ሊተካ አይገባም የሚል ፅኑ አቋም አለው። ይህም ሁኔታ የሰው ልጅ ዝርያ እንዲያከትም ያደርገዋል ይላል።

ባሕር ላይ ያለምግብና መጠጥ 11 ቀናት ያሳለፈው ኢትዮጵያዊ

ይህ ዝም ብሎ ሀሳብ ሳይሆን ፀረ-መውለድ (አንታይ ናታሊዝም) የተሰኘ ፍልስፍና ነው። ፅንሰ ሃሳቡ በጥንታዊዋ ግሪክም የነበረ ቢሆንም አሁን በማህበራዊ ሚዲያ ዘመን የበለጠ ታዋቂነትን አትርፏል።

በፌስቡክም ሆነ በሬዲት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፀረ-መውለድ ቡድን ያሉ ሲሆን አንዳንዶቹም በሺዎች የሚቆጠሩ አባላት አሏቸው። ሬዲት በተሰኘው ድረገፅ 'አር/አንታይናታሊዝም' የተሰኘ ቡድን ሰላሳ አምስት ሺ አባላት ያሉት ሲሆን በፌስቡክ ከሚገኙት አንዱ የሆነው 'ጀስት ዋን' ከስድስት ሺ በላይ አባላት አሉት።

"ወሎዬው" መንዙማ

በአለማችን ውስጥ በተለያዩ ሃገራት ተሰባጥረው የሚገኙት እነዚህ ቡድን የሰው ልጅ ማክተም አለበት ለሚለውም እምነታቸው የተለያየ ምክንያትን ይሰጣሉ።

ከነዚህም መካከል በዘር የሚተላለፍ ችግሮች፣ ህፃናት የዚህን አለም ገፈት ቀማሽ እንዳይሆኑ ለመከላከል፣ ህፃናት ለመወለድ ፈቃዳቸው ሊጠየቅ ይገባል የሚል ፅንሰ ሃሳብና አለም ላይ የህዝብ ቁጥር መጨመርና የከባቢ ደህንነት መውለድን ለመቃወም የሚያነሱዋቸው ምክንያቶች ናቸው።

ምክያቶቻቸው ቢለያይም የሰው ልጅ መዋለድንም በመቃወም ተባብረው ቆመዋል። ምንም እንኳን ይህን ያህል ተሰሚ ቡድኖች ባይሆኑም መሬትና ሃገር ላይ ባላቸው እሳቤ ተፅእኖ መፍጠር እየቻሉ ነው።

“ከተማ አስተዳደሩ የወሲብ ንግድን በህግ ወንጀል የማድረግ ስልጣን የለውም” የህግ ባለሙያ

ከዚህ ቡድን ጋር ባይያያዝም የሱሴክሱ የንጉሳዊ ቤተሰብ አባልና ባለቤታቸው ከከባቢ ደህንነት ጋር በተያያዘ የሚወልዷቸው ልጆች ከሁለት እንደማይበልጡ አሳውቀዋል።

ፍልስፍናዊ ወጎች

ቶማስ ያምንበት የነበረውን ጉዳይ "ፀረ-መውለድ' የሚል የፍልስፍና አካል መሆኑን ያወቀው ከጥቂት አመታት በፊት በዩ ቲዩብ በተሰጠ አስተያየት ምክንያት ነው። ከሰማበት እለት ጀምሮ ግን የፀረ ውልጃ ፌስቡክ ቀንደኛ ተሳታፊ ሆኗል። ምሁራዊ አስተያቶችን እንዲቃርም እንዲሁም ሃሳቦቹንም እንዲፈትሽ እድል ሰጥቶታል።

"የህይወትን እውነተኛ እክሎች ላይ ነው እያወራን ያለነው፤ ይህ አስደናቂ ነገር ነው" የሚለው ቶማስ አክሎም "የሰው ልጅ ጠፋ እንበል፤ ተመልሶ ቢመጣስ? ችግሩ አልተቀረፈም ማለት ነው" ይላል።

"በርካታ ውይይቶች አሉ፣ አንዳንዶቹ ልብ ይነካሉ" በማለት ይናገራል።

የፀረ መውለድ ፍልስፍናው በፅንሰ ሃሳብ ላይ የተመሰረተ ብቻ አይደለም። የሰው ልጅ ህይወት ትርጉም አልባ ነው የሚለውን እምነቱንም በተግባር ለመለወጥ ዜጎችን የማምከን ተግባር እንዲከናወን የብሪቴይን የጤና ማዕከልን (ኤን ኤች ኤስ) አናግሮ ነበር። ምንም እንኳን ሃሳቡ ተቀባይነት ባያገኝም

ምንም እንኳን ህይወት ትርጉም የለውም በማለት ማህበረሰቡ የሚቀበላቸውን ሞራላዊ፣ እምነታዊ፣ ባህላዊና ሌሎች እሴቶችን ባይቀበሉም ኃይልን ወይም አመፅን በመጠቀም የሰውን ልጅ እናጥፋ አይሉም። ስለ ሰው ልጅ ዘር መጥፋት የሚያወሩትም እንዲያው ለውይይት ነው። በየትኛውም ድረገፅ ላይ ሰለ መግደልም ሆነ ማስፈራራትም አይፈፅሙም።

የቶማስ አለምን የማፈንዳት ፅንሰ ሃሳብ እሱ እንደሚያስበው አንድ ቀይ ቁልፍ ነገር ቢገኝና ያንን ተጭኖ የሰውን ልጅ ድምጥማጡ ቢጠፋ የሚል ነው። ይህ እሳቤ ከራሳቸው ፅንሰ ሃሳብ ጋር የሚቃረን ነው፤ ህፃናት ለመወለድ ፍቃድ ሊሰጡ ይገባል እንደሚሉት የሚሞትም ሰው ፍቃዱ ሊጠየቅ ይገባል የሚል ነው።

በቴክሳስ ሳን አንቶኒዮ የሚኖረው ከርክ በአራት አመቱ እናቱን ለምን እንደወለደች ሲጠይቃት ምርጫ እንደሆነ በነገረችው ሰአት ግራ ያጋባው ጉዳይ እንዴት የሰው ልጅ በምርጫው ልጆች እንዲሰቃዩ ወደዚህ አለም ያመጧቸዋል የሚል ነው። የሰው ልጅ ምርጫው ተጠይቆ ወደዚህ አለም እስካልመጣ ድረስ መውለድን የሚቃወም ሲሆን እሱ ምርጫ ቢሰጠው እንደማይወለድ ይናገራል።

ነገር ግን አለም እንደነሱ በጨለምተኞች የተሞላች ብቻ ሳትሆን አለም እንድትጠፋ በማይፈልጉና በኑሯቸውም ደስተኞች የሆኑ ብዙዎች ናቸው።

ከፍልስፍናውና ከሞራል ውይይቶች በተጨማሪ ወላጆችን በማዋረድና ልጆችን በመሳደብም ይተቻሉ። "ያረገዘች ሴት ሳይ መጀመሪያ የሚሰማኝ ነገር መቀፈፍ ነው" በሚል አንድ አባል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየት ከሰጡት አንዱ ነው። ይህ ማለት ግን ሁሉም ልጆች ይጠላሉ ማለት እንዳልሆነ ቢቢሲ ያናገራቸው የፀረ መውለድ ፍልስፍና ተከታዮች ተናግረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በተጨማሪ በተለይ በጦርነት ቀጠና ያሉና ድሃ ቤተሰቦች በጭራሽ መውለድ የለባቸውም ብለው ሽንጣቸውን የሚከራከሩ ሲሆን ይህም የተመረጠ ዝርያን ያበረታታሉ የሚል ትችት እንዲቀርብባቸው ምክንያት ሆኗል።