ዛምቢያ፡ ድሮኖች ቀረጥ ያልከፈሉ ተሽከርካሪዎችን እያደኑ ነው

ከድሮኖች መካካል አንዱ Image copyright Topsy Sikalinda/ZRA

የዛምቢያ የግብር ባለሥልጣናት ቀረጥ ሳይከፍሉ እቃዎችን የሚያዘዋውሩ ከባድ መኪናዎችን ለመቆጣጠር ድሮኖችን መጠቀም ጀመሩ።

ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ የዛምቢያ ገቢዎች ባለሥልጣን በድሮኖች በመታገዝ ከዋናው መንገድ በመውጣት ተደብቀው የነበሩ ሰባት ተሽከርካሪዎች መያዛቸውን አስታውቀዋል።

ያለአብራሪ በሚበረው የሰማይ ታክሲ ይጠቀማሉ?

ሥራ ቀጣሪና አባራሪ እየሆነ የመጣው ሮቦት

" ድሮኖቹ የፍተሻ ሠራተኞች በማይደርሱባቸው እንዲሁም አደጋ ባለባቸውና ጥንቃቄን በሚጠይቁ ቦታዎች ድረስ በመግባት አሰሳ ያደርጋሉ" ሲሉ የዛምቢያ ገቢዎች ባለስልጣን የኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ ቶፕሲይ ሲካሊንዳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በዚህ ሰባት ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ሥር በዋሉበት ፍተሻ ድሮኖቹ 'ካፒሪ ስርነጅ' በተባለ መንገድ በመግባት ማሰስ የጀመሩ ሲሆን ዋናው የተሽከርካሪ መንገድ ባዶ ሆኖ አግኝተውታል፤ ከዚያም ከዋናው መስመር 14 ኪሎሜትር በሚርቅ ጥሻ ውስጥ አመላክተዋል።

Image copyright Topsy Sikalinda/ZRA
አጭር የምስል መግለጫ ከድሮኖቹ መካከል አንዷ በሥራ ላይ

በዛምቢያ ወደ ደቡብ አቅጣጫ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች በአብዛኛው ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ማላዊ፣ ወይም ታንዛኒያ የሚመጡ ናቸው።

ኃላፊው ሲካሊንዳ እንዳስታወቁት አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች በጣም በርካታ እቃዎችን ይጭኑና ወደ ፍተሻ ጣቢያው ሲቃረቡ በትንንሽ መኪና ቀንሰው ይጭናሉ ይህም ባለሙያዎቹ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገቡ ምክንያት ሆኗል።

የዛምቢያ የገቢዎች መሥሪያ ቤት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ገቢውን ለማሳደግ ተስፋ እንዳለው የቀረጥ ባለሥልጣናት ጨምረው ተናግረዋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ