ኮንጎ ለድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች የኢቦላ ክትባት ልትሰጥ ነው

የኢቦላ ክትባት ሲሰጥ Image copyright Getty Images

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላን ወረርሽኝ ለመግታት ከ60 ሺህ በላይ ለሚሆኑና በመደበኛነት ወደ ሩዋንዳና ኡጋንዳ ለሚገቡ ድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች የኢቦላ ክትባት ልትሰጥ እንደሆነ አስታወቀች።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጤና ባለሙያዎች ጥቃት ደረሰባቸው

የኢቦላ መከላከያ ክትባት በኮንጎ ሊሰጥ ነው

በሩዋንዳ ድንበር ላይ በሚገኘው የኮንጎያዊያን የንግድ ማዕከል' ጎማ' የኢቦላ ኬዝ መገኘቱን በቅርቡ አንድ ሪፖርት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ነበር ለድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎች ትኩረት መሰጠት የተጀመረው።

ባለፈው ዓመት ብቻ በኢቦላ ምክንያት በትንሹ 1900 ሰዎች ሕይወት ያለፈባት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ መከላከል አስተባባሪ የሆኑት ጂን ጃኪዩስ ሙየምቤ ከሆነ፤ በሩዋንዳ የሚገኙ የጤና ባለሥልጣናትም ድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎችን በተመለከተ ለሚደረገው የክትባት ዘመቻ 100 ሺህ ክትባቶችን ጠይቀዋል።

ይሁን እንጂ የክትባት ዘመቻው መቼ እንደሚጀመር አልታወቀም።

ኢቦላ ወደ ኡጋንዳ እየተዛመተ ነው

ዶ/ር ሙየምብ እንዳሉት ለድንበር ተሻጋሪ ነጋዴዎቹ ክትባት ከተሰጠ በኋላ የኢቦላ ታማሚ በተገኘባቸው አካባቢዎች ክትባቱን መስጠት እንደሚጀምሩ የህክምና ቡድኑ አስታውቋል።

ዓለም አቀፉን የጤና ድርጅት ጨምሮ ዓለም አቀፍ የጤና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ክትባት አገልግሎት ላይ መዋል የጀመረ ሲሆን ክትባቱ በዲሞክራቲክ ኮንጎ ግርታን ፈጥሮ ነበር።

ክትባቱ በጆንሰን እና ጆንሰን የተሰራ ሲሆን በዲሞክራቲክ ኮንጎ ባለፈው ዓመት ሲሰጥ ከነበረው ከአንድ የሜርክ ክትባት መጠን የተለየ ነው ተብሏል።

በምስራቃዊ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚዛመቱ ሀሰተኛ መረጃዎችና እምነት ማጣት ሳቢያ የኢቦላ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ገትቶታል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ