ትሬቨር ኖዋ፡ የዓለማችን አራተኛው ቱጃር ቀልደኛ

ትሬቨር ኖዋኅ Image copyright Nicholas Hunt

የተወዳጁ 'ዘ-ዴይሊ ሾው' አሰናጅና እውቁ ደቡብ አፍሪካዊ ኮማኪ ትሬቨር ኖዋ የሕይወት አጋጣሚዎቹንና ሁሉን ነገር ወደ ሳቅ በመለወጥ የሚታወቅ ኮሜዲያን ነው።

ደቡብ አፍሪካዊው ኮማኪ ትሬቨር ኖዋ እየተወገዘ ነው

ነዋሪነቱን በአሜሪካ ያደረገው ቀልደኛው ከዓለማችን ኮሜዲያን አራተኛው ከፍተኛ ተከፋይ በመሆን በዘንድሮው ዓመት የፎርብስ የዓለማችን ቱጃሮች ዝርዝር ውስጥ ስሙ ሰፍሯል።

በደቡብ አፍሪካዋ ሶዌቶ የተወለደው ትሬቨር፤ በመፅሔቱ ዝርዝር ውስጥ እስከ አስር ባሉት ደረጃዎች ውስጥ ሲሰፍር ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

የ35 ዓመቱ ትሬቨር ባለፈው ዓመት ብቻ በ 'ዘ ዴይሊ ሾው' የሚያዘጋጀው የቴሌቪዥን ፕሮግራም ጨምሮ ከተለያዩ ፕሮጀክቶች 28 ሚሊየን ዶላር ገቢ አግኝቷል።

ናይጂሪያዊው ኮሜዲያን ከአሻንጉሊት ጋር ትዳር ሊመሠርት ነው

ይሁን እንጂ ሀብቱ እያደገ የመጣው በዓለም አገራት ካካሄዳቸው 70 የሥራ ጉዞዎች ሲሆን ይህም ገቢው በቱጃር 'ስታንድ አፕ ኮሜዲያን' ዝርዝር አራተኛውን ደረጃ እንዲይዝ አስችሎታል።

ሌላኛው የገቢ ምንጩ ደግሞ በኔትፍሊክስ የሚያስተላልፋቸው ሁለት ፕሮግራሞች እንዲሁም በከፍተኛ ሁኔታ የተሸጠው 'ቦርን ኤ ክራይም ' የተሰኘው ግለ ታሪክ መፅሃፉ ነው።

በፎርብስ መፅሄት ከኮሜዲያን በአንደኝነት ስሙ የሰፈረው አሜሪካዊው ኮሜዲያን ኬቭን ኸርት ሲሆን ባለፈው ዓመት ብቻ 59 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገቢ አስመዝግቧል።

ትሬቨር አፍሪካዊያን ቱጃር ቀልደኞችን ግን በቀዳሚነት እየመራ ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ