ሩዋንዳ፡ የቢራ ፋብሪካው በጠርሙሶቹ ላይ ላተመው ፆተኛ ቀልዱ ይቅርታ ጠየቀ

የቢራ ጠርሙሶች Image copyright _

በሩዋንዳ የቢራ ፋብሪካ በቢራ ጠርሙሶቹ ላይ ባተመው ፆተኛ (ሴክሲት) ቀልዱ ይቅርታ ጠየቀ።

ስኮል በተባለው በዚህ ቢራ ጠርሙሶች ላይ " መቼ ነው አንዲት ሴት ሚሊዮነር የምታደርግህ?" የሚል ጥያቄና " አንተ ቢሊዮነር ስትሆን " የሚለውን ማስታወቂያ ቢራው ጠርሙስ ላይ ታትሞ መውጣቱን ተከትሎ ከፍተኛ ትችትን አስተናግዷል።

ፆታዊ ትንኮሳን ደርሶብኛል በማለቷ ተቃጥላ እንድትሞት የተደረገችው ወጣት

"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ"

ሌላኛው ደግሞ በፈረንሳይኛ ቋንቋ የተፃፈ ሲሆን " አንዲት ውብ ንግሥት አሳ ለመግደል የምትሞክረው እንዴት ነው? ሲል "የአሳውን ጭንቅላት ውሃ ውስጥ በመክተት " ሲል ምላሽ ይሰጣል።።

ስኮል የቢራ ጥራት ደረጃውን አሻሽሎ ካሳተመው ቀልድ ጋር ያስመረቀው ባለፈው አርብ ሲሆን ባሳለፍነው ሰኞ ምርቶቹን እንደማይጠቀም አስታውቋል።

የዓለም አቀፉ ኢኮኖሚክ ፎረም ከሦስት ዓመታት በፊት ባወጣው ሪፖርት ሩዋንዳ በሥርዓተ ፆታ እኩልነት አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

የስኮል ላጋር የብራንድ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ኢሚሌን ጠቅሶ የሩዋንዳው ጋዜጣ ኒውስ ታይምስ እንደዘገበው የቢራ ጠርሙሶቹ ላይ እንደዚህ ዓይነት ቀልዶችን ያተሙት ደንበኞቻቸው ሕይወትን ቀለል አድርገው እንዲመለከቱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የተነጠቀ ልጅነት

ይሁን እንጂ ምላሻቸው የባሰ ቁጣን ቀስቅሷል፤ አንዳንዶች እንዳውም በምርቱ ላይ አድማ ለመምታት መወሰናቸውን ገልፀው ነበር።

በጉዳዩ ላይ ቁጣቸውን ከገለፁ የሴቶች መብት ተሟጋቾ መካከል አንዷ የሆኑት የአገሪቷ የሥርዓተ ፆታ ሚንስትሯ ሶሊን ንይራሃቢማና በበኩላቸው "ቀልዶቹ ሴቶችን የሚያንኳስሱ ናቸው ፤ ምንም ተቀባይነት የለውም፤ ሊቀጡ ይገባቸዋል" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ የቢራ ጠርሙሶቹን ምስል ጨምረው አጋርተዋል።

በሩዋንዳ ቤልጅየማዊያን ድርጅት ዩኒብራ የሚመረተው ስኮል ባሳለፍነው ሰኞ በትዊተር ገፁ ላይ ይቅርታ ጠይቋል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ