የኢራን ዝነኞች፡ ከመንገድ መጨናነቅ ለመገላገል አምቡላንስ እየተጠቀሙ ነው

አምቡላንሶች በሞተር ሳይክል ተከበው የሚያሳይ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ በኢራን አምቡላንስ ከህሙማን በስተቀር ለማንኛውም ሰው መጓጓዣ እንዲውል አይፈቀድም

ለኢራን ዝነኞች የመንገድ መጨናነቅ ፈተና የሆነባቸው ይመስላል፤ ለዚህም ያዋጣናል ያሉትን መላ ዘይደዋል።

በኢራን፣ ቴህራን የሚገኙ ዝነኞችና ጥሩ ተከፋይ የግል ሠራተኞች በመዲናዋ ያለውን የመንገድ መጨናነቅ ያለምንም መጉላላት ለማለፍ አምቡላንሶችን በሕገ ወጥ መንገድ እየተጠቀሙ መሆኑን የኢራን የግል አምቡላንስ አገልግሎት ኃላፊ ገልፀዋል።

ሃዩንዳይ የሚራመድ መኪና አምርቷል

ገዳዩ የአምቡላንስ ሠራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

ሞጂታባ ሎሃራስቢ ኢስና ለተሰኘ የዜና አገልግሎት እንደተናገሩት "ክስተቱ እውነት ቢሆንም ሁኔታው ግን ብዙዎች አጋነው እንደሚሉት አይደለም" ብለዋል።

የዋና ከተማዋ አቃቤ ሕግ የአምቡላንሶችን አጠቃቀም የሚመለከቱ ሕጎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ይሁን እንጂ ዶ/ር ሎህራሲቢ እንዳሉት ፖሊስ በሥራ ተጠምዶ ስለሚውል ቁጥጥር በማድረግ ሊረዷቸው እንዳልቻሉ አስረድተዋል።

ኃላፊው አክለውም በቴህራን ከመንገድ መጨናነቅ ለመገላገል ሲሉ አምቡላንስን እንደመጓጓዣ የሚጠቀሙት ዝነኞች ብቻ እንዳልሆኑ ጠቆም አድርገው አልፈዋል፤ ሌላ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል።

ኢራናዊያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ድርጊቱን አጥብቀው የተቹት ሲሆን አንዳንዶች በስጋት ተሞልተው አምቡላንሶችን ለዚህ ተግባር የሚጠቀሙት ሰዎችን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠይቀዋል።

የኢራን ሕግ አምቡላንሶች ከህሙማን በስተቀር ለማንኛውም ሰው መጓጓዣ እንዲውሉ አይፈቀድም።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ