በስፔን ከ550 በላይ የሚሆኑ ሴቶችን የተጋለጠ አካል የሚያሳይ ቪዲዮ የቀረፀው ተከሰሰ

አብዛኛዎቹ ሴቶች ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በማድሪድ ሜትሮ ነው Image copyright Reuters
አጭር የምስል መግለጫ አብዛኛዎቹ ሴቶች ጥቃቱ የተፈፀመባቸው በማድሪድ ሜትሮ ነው

በስፔን ማድሪድ ከ550 በላይ የሚሆኑ ሴቶችን የተጋለጠ አካል የሚያሳይ ቪዲዮ ያለፈቃዳቸው በመቅረፅ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ። ግለሰቡ ሴቶቹን ቪዲዮ ከቀረፃቸው በኋላ አብዛኛውን በድረገፆች ላይ አሰራጭቶታል ተብሏል።

ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ?

ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና

የ53 ዓመቱ ኮሎምቢያዊ ግለሰብ ተንቀሳቃሽ ምስሉን የቀረፀው በጀርባው ባዘለው ቦርሳው ውስጥ በደበቀው ተንቀሳቃሽ ስልኩ ነው።

ፖሊስ እንዳስታወቀው 283 የሚሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የወሲብ ፊልሞች በሚተላለፉባቸው ድረ ገፆች ላይ የጫነው ሲሆን በሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች ተመልክተውታል።

ጥቃቱ ከተፈፀመባቸው 555 ሴቶች መካከል ህፃናትም ይገኙበታል።

'የተሳመው ከንፈር' ጥቃት ደረሰበት

ግለሰቡ የቀረበበት ክስ እንደሚያስረዳው ተንቀሳቃሽ ምስሎቹን በድረገፆች ማሰራጨት ከጀመረበት ባለፈው ዓመት አንስቶ ድርጊቱን የዕለት ተዕለት ሥራው አድርጎት ነበር።

ከዚህም ባሻገር ድርጊቱን በገበያ ማዕከላት አንዳንዴም ደግሞ ጥራት ያለው ምስል ለማግኘት እንዲያስችለው ቆም ብሎ ራሱን በማስተዋወቅ ይቀርፅ እንደነበር ተነግሯል።

በሜትሮ አንዲት ሴትን በመቅረፅ ላይ ሳለ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለው ተጠርጣሪ ምርመራ እየተካሄደበት ነው።

የአገሪቷ ፖሊስም በትዊተር ገፅ ላይ በተሰራጨ ተንቀሳቃሽ ምስል ሥር ተጠርጣሪውን " የሴቶችን ግላዊ መብት የጣሰ ቀንደኛ ወንጀለኛ" ሲሉ ገልፀውታል።

ፖሊስ የግለሰቡን ቤት ፍተሻ ባደረገበት ወቅት ላፕቶፖችንና የፋይል ማስቀመጫ [ሃርድ ድራይቭ] ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቪዲዮዎችን አግኝቷል። በግለሰቡ ስም የተከፈተው ድረ ገፅም 3 ሺህ 519 ተከታዮች አሉት።

በስፔን የሴቶች አካል ያለፈቃዳቸው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል፣ ፎቶ ማንሳት እንደ ወሲባዊ ጥቃት የሚቆጠር ሲሆን በእስራት ያስቀጣል።

በእንግሊዝና ዌልስም በደራሲ ጊና ማሪን ከተካሄደ ዘመቻ በኋላ የሴቶችን አካል ያለፈቃዳቸው የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስልም ሆነ ፎቶ ማንሳት ወንጀል ሆኖ ተደንግጓል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ