ታንዛኒያዊው ጋዜጠኛ በ'ሀሰተኛ ዜና' ታሰረ

ጋዜጠኛ ጆሴፍ

ታንዛኒያዊው ጋዜጠኛ 'ፖሊስ በእስር ቤት የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን ያሰቃያል' በሚል የሰራው ዘገባ 'ሀሰተኛ ነው' በሚል ለእስር መዳረጉ ተገለፀ። ጋዜጠኛ ጆሴፍ በታንዛኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥምረት በተቋቋመው ዋቴቴዚ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው የሚሰራው።

ፌስቡክ የአፍሪካ የዴሞክራሲ ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ነው?

ኻሾግጂ የዓመቱ ምርጥ ሰው ዝርዝር ውስጥ ተካተተ

የቴሌቪዥን ጣቢያው የጋዜጠኛውን መታሰር አጥብቆ ያወገዘ ሲሆን በትዊተር ገፁ ላይ ጋዜጠኛው በዚህ ወር መጀመሪያ ሪፖርቱን አጠናቅሮበት ወደነበረው ኢሪንጋ መወሰዱን አስታውቋል።

ጣቢያው እንዳለው ከሆነ የኢሪንጋ ፖሊስ የተሰራውን ዘገባ አስመልክቶ " ሀሰተኛና አሳሳች ሪፖርት ሲሆን የታንዛኒያን የፖሊስ ኃይል እና መንግሥትን የሚያጣጥል ነው" ሲል ማስጠንቀቂያ አዘል ምላሽ ሰጥተዋል።

"ለደህንነት ኃላፊው አሳሳችና ሀሰተኛ ዜና የሚያሰራጩ ሰዎችን እንዲከታተሉ ትዕዛዝ አስተላልፌያለሁ፤ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላም ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል " ማለታቸውን የቴሌቪዥን ጣቢያው የአካባቢውን ፖሊስ ጠቅሶ ዘግቧል።

ከአንድ ወር በፊት በዚያው ታንዛኒያ ታዋቂው የምርመራ ጋዜጠኛው ኤሪክ ካቤንደራ ለእስር ተዳርጎ ነበር።

ጋዜጠኛው በእስር ላይ ሳለ በተፈፀመበት የሰብዓዊ መብት ጥሰትም በአገሪቷ የሚገኙ የአሜሪካና የእንግሊዝ ኤምባሲዎችን ትኩረት ስቦ ነበር።

ፕሬዚደንት ጆን ማጉፋሊ በቅፅል ስማቸው 'ዘ ቡልዶዘር' በአውሮፓዊያኑ 2015 ሥልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ ለሚዲያና የሚዲያ ባለሙያዎች ፈታኝ እንደሆነባቸው ይነገራል።

ጋዜጦች እና የራዲዮ ጣቢያዎችም ሕግ ጥሰዋል በሚል ሰበብ መታገዳቸው ተጠቅሷል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ