ፖላንድ፡ በታራ ተራራ በጣለ መብረቅ አራት ሰዎች ሲሞቱ መቶ ጉዳት ደረሰባቸው

ተጎጅዎች በሄሊኮፕተር ሲወሰዱ Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ጉዳት ያጋጠማቸው ሰዎች በሄሊኮፕተር ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

በፖላንድ በጣለ መብረቅ በትንሹ አራት ሰዎች ሲሞቱ ከመቶ በላይ የሚሆኑት ጉዳት እንዳጋጠማቸው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ማቴውዝ ሞራዌኪ ገለፁ።

"ከተራራው ሰዎች ሲወድቁ አይቻለሁ" ሲራክ ስዩም

በክረምት ሲዘንብ የመሬት ሽታ ለምን ያስደስተናል?

በፖላንድ ደቡባዊ ክፍል በሚገኝ ጊዎንት በተባለ እውቅ ተራራ በቡድን ሆነው ተራራውን በመውጣት ላይ የነበሩ ሰዎች ላይ መብረቅ ጥሎ ሞትና ጉዳት እንዳስከተለ ነው የተነገረው።

ይህ አደገኛው ክስተት ያጋጠመው ባሳለፍነው ሐሙስ ሲሆን ከባህር ጠለል በላይ 1894 ሜትር ከፍታ ባለው ጌወንት ተራራ ላይ ነው።

በዚያው ተራራ አቅራቢያ ስሎቫኪያ፤ ሌላ አንድ ሰው ሕይወቱ ያለፈ ሲሆን ከሞቱት መካከል አንደኛው ሕፃን ነው ተብሏል። መብረቁ ጠዋት ላይ ከነበረው ፀሐይ በኋላ ድንገት የጣለ ከባድ ዝናብን ተከትሎ ነበር የተከሰተው።

"እንዲህ ዓይነት አደጋ ይከሰታል ብሎ ማንም ሰው አልጠበቀም፤ ድንገት ነበር የሆነው፤ እንደ ሰው፤ እንዲህ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው" ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ በአካባቢው በተደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

በተለያዩ የተራራው አካባቢ ተመሳሳይ ጉዳት ማጋጠሙ የተነገረ ሲሆን አራት የነፍስ አድን ሄሊኮፕተሮች ወደ አካባቢው ተልከዋል።

"አስደንጋጩን የመብረቅ ድምፅ ሰማን ፤ ሰዎች ወደቁ፤ ከዚያም በመንገዱ ላይ የነበሩ ሰዎችን መምታት ጀመረ፤ በጣም የሚዘገንን ነበር" ሲሉ የተራራው አደጋ መከላከል ኃላፊ ጃን ክርይስዝቶፍ ፒኤፒ ለተሰኘው የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ስለ ነበረው ሁኔታ ገልፀዋል።

የዛኮፓኔ ከንቲባ ልስዜክ ዶሩላ ዛሬ የሐዘን ቀን ሆኖ እንዲውል አውጀዋል።

በታትራ አካባቢ ዛኮፓኔ ከተማ የሚኖር አንድ የአይን እማኝ የመብረቁን አደጋ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምሥልም አጋርቶት ነበር።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ