የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሲብ ንግድን ማገድ ለምን አስፈለገው?
የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሲብ ንግድን ማገድ ለምን አስፈለገው?

ከሰሞኑ የአዲስ አበባ አስተዳደር የጎዳና ልመናና የወሲብ ንግድን ለማገድ ረቂቅ ሕግ ማዘጋጀቱን ተከትሎ በብዙዎች ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። ከእግዱ አላማ አንስቶ እስከተደረጉ ዝግጅቶች፣ እንዲሁም የአስተዳደሩ ሥልጣን ባሉና በተያያዙ ጉዳዮች ውይይቶች ቀጥለዋል።

ረቂቅ ሕጉ በአሁኑ ወቅት ለካቢኔ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ብቻውን መወሰንም ስለማይችል ባለድርሻ አካላት በተለይም የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተያየት እንዲሰጡበትም እየተደረገ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ፌቨን ተሾመ አስረድተዋል።