በእርግጥ የእንግሊዙ ጠ/ሚ እግራቸውን የገበታ ጠረጴዛ ላይ ሰቅለዋል?

ቦሪስና ማክሮን፡ቦሪስ እግራቸውን ጠረጴዛ ላይ ሰቅለው ይታያሉ Image copyright Reuters

ቦሪስ ጆንሰን አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው።

አንዳንዶች "እንግሊዛዊው ዶናልድ ትራምፕ" ይሏቸዋል።

ወደ መንበሩ ከመጡ በኋላ ታዲያ የጀርመኗን መራሒተ መንግሥት አግኝተዋል። በነገታው ደግሞ ፓሪስ ነበሩ። ከማክሮን ጋር ቁጭ ብለው ሲጨዋወቱ ቦሪስ አንድ ክብ ጠረጴዛ ላይ እግራቸውን ሲሰቅሉ የሚያሳይ ፎቶ ዓለምን አዳርሷል። ሰውየው የመሪን ክብር የማይመጥን አስነዋሪ ድርጊት ፈጽመዋል በሚልም እየተወገዙ ነበር።

እንግሊዝ "ራስን የማጥፋት" ተከላካይ ሚኒስትር ሾመች

100 ሺህ ብር፤ ብልትን ለማወፈር

በእርግጥ የሆነው ምንድነው? ለምንስ ጫማቸውን ጠረጴዛ ላይ ሰቀሉ?

ያን ድርጊት ለቅጽበት ያደረጉት ማክሮን ቀልድ እያወሩላቸው ስለነበረ ከዚያ ጋር በተያያዘ እንደሆነ መረጃዎች ወጥተዋል።

"ይሄ ወንበር ድሮ እግር መስቀያም ሆኖ አገልግሏል" ሲሉ በጨዋታ መልክ ነገሯቸው፤ ማክሮን ለቦሪስ። በዚህን ጊዜ ቦሪስ «ኦ ነው እንዴ!» ብለው ጫማቸውን ጠረጴዛው ላይ ሰቀሉ፤ በቀልድ መልክ።

ያም ሆኖ ብዙዎች በቦሪስ ድርጊት ተበሳጭተው በትዊተር ሰሌዳ በጻፉት መልእክት «ጠቅላይ ሚኒስትሩን ግብረ ገብ አልተማሩም» ብለዋል።

ሌላ የፈረንሳይ ዜጋ ደግሞ «ንግሥቲቱ ይህንን ስታይ ምንድነው የሚሰማት?» ሲል ጽፏል።

የቀድመው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌይር ቀኝ እጅ የነበሩት አላስተር ካምፔል በበኩላቸው «አሳፋሪ ድርጊት ነው። ቦሪስ የእንግሊዝና የፈረንሳይ መሪዎችን ለማግኘት ይህን ያህል ከቆየ በኋላ ጫማውን ሰው ጠረጴዛ ላይ ይሰቅላል?» ሲሉ መናገራቸውን ፒኤ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ወንበር የሚለቅላት አጥታ ልጇን ቆማ ያጠባችው እናት

"ነገሩ ተራ ጉዳይ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን የሰውየውን እብሪተኝነትና ንቀትን ነው የሚያሳየው" ብለዋል ካምፔል ጨምረው።

ከዚህ ሁሉ በኋላ የነገሩን ሌላ መልክ ለማሳየት የሞከረው የስካይ ኒውስ የፖለቲካ ዘጋቢ ቶም ራይነር ነበር።

"ሁለቱ መሪዎች እየተቀላለዱ ነበር። ማክሮን «ይሄ ጠረጴዛ እግር ማሳረፊያ ሆኖም ያገለግላል» ሲሏቸው ቦሪስ ጫማቸውን ሰቀሉበት"ብሏል።

አንዳንድ የፈረንሳይ መገናኛ ብዙኃን ነገር አብርዱ ሲሉ ጽፈዋል።

«በፍጹም ቦሪስ ማክሮንንም ሆነ ፈረንሳይን አልተሳደቡም። ድሮም ኢንተርኔት ነገሮችን ከአውድ ውጭ እያወጣ ያራግባል» ሲል ጽፏል ሌ ፓርሺያን የተሰኘ አንድ የፈረንሳይ ጋዜጣ።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ