ናሳ ህዋ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጀል ተፈጸመ አለ

አን ማክሌን Image copyright Reuters

አን ማክሌን ጠፈርተኛ ናት። ከምድር ብዙ ርቀት ተጉዛ ህዋ ላይ የምትገኘው አን፤ በጠፈር ምርምር ታሪክ ህዋ ላይ ሳለች ወንጀል የሠራች የመጀመሪያዋ ግለሰብ መሆኗን ናሳ ይፋ አድርጓል።

ጠፈርተኛዋ ከፍቅር ጓደኛዋ ጋር ከተቃቃረች ቆየት ብሏል። ህዋ ላይ መሆኗ ታዲያ የቀድሞ ወዳጇን የባንክ አካውንት ከመፈተሽ አላገዳትም።

አን የቀድሞ ወዳጇን የባንክ አካውንት መፈተሿን ብታምንም፤ "ምንም አላጠፋሁም" ማለቷን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል። አን እና ስመር እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2014 ትዳር መስርተው፤ 2018 ላይ ተለያይተዋል።

ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት?

የቀድሞ ወዳጇ ስምር ዎርደን ጉዳዩን ለንግድ ኮሚሽን ሪፖርት ካደረገ በኋላ፤ ጠፈርተኛዋ ወደ መሬት ተመልሳለች።

አን በጠበቃዋ በኩል ለኒዮርክ ታይምስ እንደተናገረችው፤ የስመርን የባንክ አካውንት የፈተሸችው አብረው ሳሉ በጋራ ያሳድጉት የነበረውን የስምር ልጅ የሚያስተዳድርበት በቂ ገንዘብ እንዳለው ለማወቅ ነበር።

ጠበቃዋ ረስቲ ሀርዲን "አንዳችም ጥፋት የለባትም" ሲሉ ተደምጠዋል።

በ2024 እቃና ሰው ጫኝ መንኮራኩር ወደጨረቃ ይላካል ተባለ

ናሳ ጉዳዩን ከሁለቱም ግለሰቦች እያጣራ እንደሚገኝ ለኒውዮርክ ታይምስ ገልጿል።

አን 2013 ላይ ናሳን ከመቀላቀሏ በፊት ለ800 ሰዓታት የጦር አውሮፕላን ወደ ኢራቅ አብርራለች። ናሳ ሙሉ በሙሉ ሴቶች ያሳተፈ የህዋ ጉዞ ለማድረግ ባቀደበት ወቅት ከተካተቱ ጠፈርተኞች አንዷ ናት። ሆኖም ናሳ "ለጠፈርተኞቹ የሚሆን ልብስ አላዘጋጀሁም" ብሎ ጉዞው መሰረዙ ይታወሳል።

ለመሆኑ ህዋ ላይ ሕግ የሚተገበረው እንዴት ነው?

የህዋ ማዕከሉ ባለቤቶች አሜሪካ፣ ሩስያ፣ አውሮፓ፣ ጃፓን እና ካናዳ ናቸው። አንድ ሰው ወንጀል ቢፈጽም የሚጠየቀው በአገሩ ሕግ ነው።

ለመብረር የተዘጋጁት ልጃገረዶች

አንድ አገር ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረውን ግለሰብ በሌላ አገር ሕግ ለመዳኘት ከወሰነች፤ ግለሰቡ ወደ ምድር እንዲመለስ ከተደረገ በኋላ ለፍርድ ይቀርባል።

ከዚህ ቀደም ህዋ ላይ ወንጀል ተሠርቶ ስለማያውቅ የህዋ ሕግ ተግባራዊ የሚሆንበት እድል አልነበረም። ምናልባትም ቱሪስቶች ህዋን መጎብኘት ሲጀምሩ ሕጉን መተግበር ይጀመር ይሆናል።

ተያያዥ ርዕሶች