ስካርሌት ጆሃንሰን፡ የዘንድሮው የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ ተዋንያን እነማን ናቸው?

ተዋናይት ስካርሌት ጆንሰን Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በዘንድሮው የፎርብስ የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ 10 ተዋንያን ውስጥ ሁለት ሴቶች ይገኙበታል

በዘንድሮው የፎርብስ ከፍተኛ ተከፋይ ተዋንያን ዝርዝር ውስጥ በሴቶቹ ዘርፍ አሜሪካዊቷ ተዋናይና አዘጋጅ ስካርሌት ጆሃንሰን አንደኛ ደረጃን ተቆናጥጣለች።

የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ ተዋናዮች ዝርዝር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ስሟ የሰፈረ ሲሆን በአጠቃላይ አሥር ተዋንያን ዝርዝር ውስጥ ደግሞ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን?

የ34 ዓመቷ ተዋናይት ስካርሌት ጆሃንሰን ያስመዘገበችው 56 ሚሊን ዶላር ሰባተኛ ደረጃ ከያዘው ወንድ ተዋናይ አዳም ሳንድለር ጋር ይስተካከላል።

በ'ሞደርን ፋሚሊ' ተከታታይ ፊልም ላይ የምትተውነው ሶፊያ ቨርጋራ ደግሞ ከአሥሩ የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ ተዋናያን ሁለተኛዋ ሴት ሆናለች።

ባላፉት 12 ወራት 89.4 ሚሊየን ዶላር በማስመዝገብ አሜሪካዊው ተዋናይ ድዋይን ጆንሰን [ዘ ሮክ] ከፍተኛ ተከፋይ ተዋናይ በመሆን ቀዳሚነቱን ይዟል።

ከ1-10ኛ ደረጃ የያዙት ተዋንያን በዚህ ዓመት ከ20 ሚሊየን ዶላር በላይ ያስመዘገቡ ሲሆን ባለፈው ዓመት የመጀመሪያዎቹን ሁለት ደረጃዎች የተቆናጠጡት ስካርሌት ጆሃንሰንና አንጀሊና ጆሊ ብቻ ነበሩ።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሶፊያ ቬርጋራ፣ ጀኔፈር አኒስተን እና ማርጎት ሮቤ [ ከግራ ወደ ቀኝ]

ባለፈው ዓመት አንጀሊና ጆሊ 28 ሚሊየን ዶላር ብታስመዘግብም በዘንድሮው አሥሮች ዝርዝር ውስጥ መግባት አልቻለችም።

አንጀሊና በአሁኑ ሰዓት "ሚስትረስ ኦፍ ኢቪል" እና "ዘ ዋን ኤንድ ኦንሊ ኢቫን" የተሰኙ ሁለት አዳዲስ ፊልሞች ላይ እየተወነችና እያዘጋጀት ትገኛለች።

በዚህ ዓመት ዝርዝር ውስጥ ካልተካተቱ ተዋንያን መካከል ሚላ ኩኒስ፣ ጁሊያ ሮበርት፣ ሜሊሳ ምካቲይ እና ጋል ጋዶት ይገኙበታል።

የምርጥ ተዋናይቷን ኦስካር ሽልማት የሰረቀው በቁጥጥር ስር ዋለ

የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ

በዘንድሮው የከፍተኛ ተካፋይ ተዋንያን ዝርዝር፤ ከወንድ ተዋንያን ዝርዝር በስተቀር በሴቶቹ ዘርፍ ብዙም ስብጥር አልታየም፤ ሶፊያ ቬርጋራ ኮሎምቢያዊ አሜሪካዊት ስትሆን በዝርዝሩ ውስጥ ጥቁር አሜሪካዊ ተዋንያን አልነበሩም።

የዘንድሮየዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ ሴት ተዋንያን

1. ስካርሌት ጆሀንሰን [56 ሚሊየን ዶላር]

2. ሶፊያ ቬርጋራ [44.1 ሚሊየን ዶላር]

3. ሪስ ዊዘርስፑን [35 ሚሊየን ዶላር]

4. ኒኮል ኪድማን [34 ሚሊየን ዶላር]

5. ጀኔፈር አኒስተን [28 ሚሊየን ዶላር]

6. ካሌይ ኩኮ [25 ሚሊየን ዶላር]

7. ኤልዛቤት ሞስ [24 ሚሊየን ዶላር]

8. ማርጋሬት ሮቤ [23.5 ሚሊየን ዶላር]

9. ቻርሊዝ ቴሮን [23 ሚሊየን ዶላር]

10. ኤለን ፖምፔዎ [22 ሚሊየን ዶላር]

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አሜሪካዊው ተዋናይ ድዋይን ጆንሰን (ዘ ሮክ)

ፎርብስ የዓለማችን ከፍተኛ ተከፋይ ወንዶች ተዋናይ ዝርዝርም ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ይፋ አድርጓል።

ዘ ሮክ በሚለው ቅፅል ስሙ የሚታወቀው አሜሪካዊው ተዋናይና ዳሬክተር ድዋይን ጆንሰን ምንም እንኳን ባለፈው ዓመት አስመዝግቦት ከነበረው 119 ሚሊየን ዶላር ዝቅ ቢልም፤ ከነበረበት ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ብሎ አንደኛነትን ይዟል።

ዕውቁ አሜሪካዊው ተዋናይ ዘ ሮክ በሚስጢር ተሞሸረ

ባለፈው ዓመት በፎርብስ ዝርዝር ውስጥ አንደኛ ሆኖ የተመዘገበው ጆርጅ ክሉኒ ግን በዘንድሮው አሥሮቹ ዝርዝር ውስጥ መግባት አልቻለም።

ምክንያቱም ባለፈው ዓመት አስመዝግቦት ለነበረው ከፍተኛ ገንዘብ አስተዋፅኦ ያደረገለት እና 1 ቢሊየን ዶላር የሚገመተው የአልኮል ማምረቻ ድርጅቱ በመሸጡ ገቢው በማሽቆልቆሉ ነው።

በዝርዝሩ፤ ሁሉም ዝነኞች ከማስታወቂያ እና ትወና በተጨማሪ ከሌሎች የገቢ ምንጮች የሚያገኙትንም ገቢ ያማከለ ነበር።

በዚህ ዓመት የፎርብስ ከፍተኛ ተከፋይ ተዋንያን ዝርዝር ሁለተኛ ደረጃን የያዘው ክሪስ ሄመንስዎርዝ ሲሆን 76.4 ሚሊየን ዶላር አስመዝግቧል።

ብራድሊ ኩፐር ከአራት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሥሮቹ ዝርዝር ውስጥ ስሙ ሰፍሯል። ብራድሊ በደራሲነት፣ በአዘጋጅነትና፣ በረዳት አዘጋጅነት የኦስካር ሽልማት አግኝቶ ነበር፤ በዚህ ዓመትም 57 ሚሊየን ዶላር በማስመዝገብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ባለፈው ዓመት 'አላዲን ' በተሰኘው ፊልም ብቻ የታየው ዊል ስሚዝ በዚህ ዓመት ገቢው ተቀዛቅዞበታል። ያስመዘገበውም 35 ሚሊየን ዶላር ነው።

የቦሊውዱ ኮከብ አክሳይ ኩማር አስገራሚ ለውጥ ያሳየ ተዋናይ ሆኖ 65 ሚሊየን ዶላር በማስመዝገብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የዘንድሮከፍተኛ ተከፋይ ወንድ ተዋንያን ዝርዝር

  1. ዱዋይን ጆንሰን [89.4 ሚሊየን ዶላር]
  2. ክሪስ ሄምስወርዝ [76.4 ሚሊን ዶላር]
  3. ሮበርት ዶውኒይ [66 ሚሊን ዶላር]
  4. አክሻይ ኩማር [65ሚሊየን ዶላር]
  5. ጃኪ ቻን [58 ሚሊየን ዶላር]
  6. ብራድሊ ኩፐር [57 ሚሊየን ዶላር]
  7. አዳም ሳንድለር [57 ሚሊየን ዶላር]
  8. ክሪስ ኢቫንስ [43 ሚሊየን ዶላር]
  9. ፖል ሩድ [41 ሚሊየን ዶላር]
  10. ዊል ስሚዝ [35 ሚሊየን ዶላር]

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ