ኬንያ በህዝብና በቤት ቆጠራው ምክንያት መጠጥ ቤቶችና የምሸት ክበቦች አገልግሎት እንዲያቋርጡ አደረገች

የህዝብና ቤት ቆጠራ Image copyright SIMON MAINA

የኬንያ ሃገር አቀፍ የህዝብና ቤት ቆጠራ በትናንትናው ዕለት ነሐሴ 18፣ 2011ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፤ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅም 140ሺ ፖሊሶችን አሰማርታለች።

በትናንትናው እለት በተጀመረው የህዝብና የቤት ቆጠራው ምክንያት መጠጥ ቤቶች፣ ሬስቶራንቶችና የምሽት ክበቦች ለሁለት ቀናት ያህልም አመሻሹ ላይ ምንም አይነት አገልግሎት እንዳይሰጡም ትእዛዝ ተላልፎባቸዋል።

የሕዝብ ቆጠራው መራዘም ያስከተለው ቅሬታና የኮሚሽኑ ምላሽ

አምስት ነጥቦች ስለቀጣዩ የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ

ኬንያ ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነፃነቷን ከተጎናፀፈች በኋላ የተደረገው ስድስተኛ ቆጠራ ሲሆን ለሳምንት ያህልም እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

በመላው አገሪቱ በሚካሄደው በዚህ የህዝብና ቤት ቆጠራም ለማሳለጥ የተቀጠሩ ሰራተኞች ታብሌቶቻቸውን ይዘው በየቤቱ በማንኳኳት ቆጠራቸውን በማከናወን ላይ ናቸው።

የሃገሪቱ ሚዲያዎች እንደዘገቡት በዚህ ቆጠራም ያልተለመዱ ጥያቄዎች ለምሳሌም ያህል በወር ለውሃና ለመብራት አገልግሎት የሚያወጡት ገንዘብ መጠን፣ ባጃጅ እንዲሁም የቤት እንስሶች አላችሁ ወይ የሚል ጥያቄን እንደተጠየቁ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በባለፉት አስራ አምስት አመታት ከሃገር ውጭ ተጉዘው እንደሆነ፣ በባለፈው አመት ልጅ ሞቶባቸው ከሆነ፣ ምን ያህል ወንድ ልጆች አላችሁ የሚሉና ብዙዎችን ግራ ያጋቡ ጥያቄን እንደተጠየቁ ተዘግቧል።

የሌሉት 350 ሚሊዮን ሠዎች

ቆጠራው በተጀመረበት እለትም የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሰጡት መግለጫ የህዝብና ቤት ቆጠራው ሃገሪቷ ላቀደችው የልማት ፕሮግራሞች ግብዓት ስለሆነ ህዝቡ ትክክለኛውን መረጃ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ የሚቀጥለው ምርጫ ተፅእኖ ለመፍጠርና የመራጮቻቸውን ቁጥር ለመጨመር በሚል ፖለቲከኞች ህዝቡን ወደሚወክሉት አካባቢ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት እንዳያጓጉዙ ቀጠን ያለ ትእዛዝ ባለስልጣኖቿ አስተላልፈዋል።

ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ለሚካሄደው ምርጫ 3.7 ቢሊዮን ብር ጠየቀ

በዚህ የህዝብና የቤት ቆጠራም ላይ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለቱ የፆታ ምድብ ውስጥ የማይካተቱ 'ኢንተርሴክስ' የማህበረሰቡ አካላት ብሄራዊ የህዝብ ቁጥር ውስጥ ይካተታሉ። ይህም ለሰብዓዊ መብት ታጋዮች ትልቅ ድል ነው ተብሏል።

በከፍተኛ ሙስና ቅሌቶች በምትታማው ኬንያ ለህዝብ ቆጠራው የተያዘው 180 ሚሊዮን ዶላር ጥያቄዎችንም አጭሯል።

ከዚህም በተጨማሪ በኬንያ መረጃን የመጠበቅ ህግ ይህንን ያህል የጠበቀ ስላልሆነ ግላዊ መረጃዎች ሊጋለጡ ይችላሉ የሚልም ስጋት ሞልተውታል።

ተያያዥ ርዕሶች