በአውሮፕላን ውስጥ ለቀልድ "ቦምብ" ያለው ኢትዮጵያዊ ለእስር ተዳረገ

የኬንያ አየር ማረፍያ Image copyright SIMON MAINA

በአውሮፕላን ውስጥ ሆነው ቀልድ ቢናገሩ እንዲያው መዘዝ የሚያስከትልብዎት መስሎዎት ያውቃል? 'በለፈለፉ ይጠፉ' እንዲሉ አንድ ኢትዮጵያዊ አውሮፕላን ውስጥ ሆኖ በቀልድ መልኩ ቦምብ ማለቱ ለአራት ወራት እስር ዳርጎታል።

ጪፍራየ በቀለ ሚያዝያ ወር ላይ ከናይሮቢ ወደ ጆሃንስበርግ ለመብረር "ቦምብ" ብሎ በመቀለዱ የጆሞ ኬንያታ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለሦስት ሰዓታትም ያህል ተዘግቷል።

ፖሊስ አንድን ወጣት ሲደበድብ በተንቀሳቃሽ ምስል ያስቀረው የዐይን እማኝ

ኢትዮጵያውያን 'የሌሉበት' ስለ ኢትዮጵያ የሚዘክረው ሬድ ሲ ዳይቪንግ ሪዞርት ፊልም

ቢቢሲ ከውሳኔው እንደተረዳው ጪፍራየ በቀለ አውሮፕላን ውስጥ የበረራ አስተናጋጆች እየተቆጣጠሩ ባሉበት ሰዓት "ምን ያስፈራል? ቦምብ መሰለሽ ወይ" በማለት ለበረራ አስተናጋጇ በመቀለድ ተናግሯል።

የበረራ አስተናጋጇም የሥራ ባልደረቦቿን ካዋየች በኋላ ለአብራሪው በመናገር አውሮፕላኑ ሌላ ቦታ ተወስዶ ሁሉም መንገደኞች እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ አውሮፕላኑ ተፈትሿል። በረራውም ተሰርዟል።

ለወራት ማረፊያ ቤት በእስር ላይ የቆየው ኢትዮጵያዊ አርብ እለት ፍርድ ቤት ቀርቦ እስር ተበይኖበታል።

የኢትዮጵያዊው ንግግር አዲስ ክስተት አይደለም፤ ከዚህ ቀደምም እንዲህ አይነት ሁኔታዎች አጋጥመው ያውቃሉ። ከስድስት ዓመታት በፊትም በጆን ኤፍ ኬኔዲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አንድ ግለሰብ ለጓደኛው "ቦምብ" ሲል የሰማው የደህንነት ሰራተኛ ግለሰቡን በቁጥጥር ሥር አውሎታል።

ግለሰቡ የጠራው 'ቦምብ' የሚል መጠሪያ ስላለው ታዋቂ ሳንድዊች ነበር።

በጎርጎሳዊያኑ አቆጣጠር 2004ም እንዲሁ እንግሊዛዊ ተማሪ ቦርሳዋ ውስጥ 'ቦምብ' እንዳለ በመቀለዷ በአሜሪካ አየር ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋለች ሲሆን ለቀልዱም ይቅርታ ጠይቃለች።

እንደ ጎርጎሳውያኑ 2003ም እንዲሁ የኢራቅ የባህር መርከበኛ ሁለት ቦምቦችን በሻንጣው ይዣለሁ ማለቱን ተከትሎ የፀጥታ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር ተዘግቧል።