አፕል iPhone 11 Pro የተሰኘ አዲስ ምርቱን ይፋ አደረገ

iPhone 11 Pro Image copyright Apple

አፕል የተለያዩ የiPhone 11 ምርቶቹን ይፋ አደረገ። አዲሶቹ የአፕል iPhone 11 ምርቶች የተሻለ ካሜራ እና በአነስተኛ የባትሪ ኃይል የሚሰሩ ፈጣን ፕሮሰሰር ተግጥሞላቸዋል ተብሏል።

አፕል iPhone XS Max እና iPhone XS ስልኮቹን ይፋ ያደረገው የዛሬ ዓመት ገደማ ነበር።

አዲሶቹ iPhone 11 ምርቶች የጀርባ ካሜራ "ultrawide" የተሰኘ በፎቶ ሰፊ አካባቢን መሸፈን የሚያስችል አማራጭ አላቸው። ከዚህ በተጫመሪም የጀርባ ካሜራዎቹ አንድን ቁስ ሁለት እጥፍ በማቅረብ ፎቶግራፍ ማንሳት ያስችላሉ።

አይፎን አዲስ ስልኮችን ይዞ ብቅ ብሏል

አፕል ቲቪ ጀመረ

iPhone 11 ከአንድ ዓመት በፊት ይፋ ከተደረገው iPhone XR በዋጋ የሚያንስ ሲሆን፤ iPhone 11 Pro የተሰኘው ሞዴል ግን ወደ 55ሺህ ብር ያስወጣል።

ጉግል፣ ሳምሰንግ እና ሁዋዌ የተሰኙ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አፕል ከሚያመርታቸው ስልኮች ጋር ተቀራራቢ አማራጮችን ለደንበኞች በማቅረብ የዘመናዊ ስልክ ገብያ ተፎካካሪነታቸው እንደቀጠለ ነው።

ከስልኮቹ በተጨማሪ አፕል ዘመናዊ የእጅ ሰአቶችንም ይፋ አድርጓል። አዲሶቹ ሞዴሎች እስክሪናቸው እንደበራ እንዲቆይ የሚያስችል አዲስ "always on" የተባለ አማራጭን አካተዋል።

Image copyright Apple
አጭር የምስል መግለጫ አዲሱ የአፕል የእጅ ስልክ ከ10 ቀናት በኋላ ለገብያ ይቀርባል ተብሏል።

5ኛ ስሪት የሆኑት የእጅ ሰዓቶች አቅጣጫ መጠቆሚያ ኮምፓስ የተገጠመላቸው እና የወር አበባ ዑደትን መከታተል የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል። በተጨማሪም አዲሱ የአፕል የእጅ ሰዓቶች ረዥም የባትሪ እድሜ እንዳላቸው ተነግሮላቸዋል።

አዲሶቹ የአፕል የእጅ ሰዓቶች ከ10 ቀናት በኋላ ለገብያ ሲቀርቡ እስከ 5800 ብር ድረስ ይጠየቅባቸዋል ተብሏል።

አይዲሲ የተባለ ጥናት የሚያካሂድ ተቋም እንደሚለው ከሆነ አፕል ከጠቅላላው የዘመናዊ ስልኮች ገብያ 49 በመቶ የሚሆነውን ተቆጣጥሮ ይዟል።