በጠርሙስ በላኩት መልዕክት ሕይወታቸው የተረፈው ቤተሰብ

በሕይወት የተረፈው ቤተሰብ Image copyright CBS - Newspath video
አጭር የምስል መግለጫ በሕይወት የተረፈው ቤተሰብ

አሜሪካ ውስጥ ባላሰቡት ሁኔታ የውሃ ፏፏቴ ውስጥ ገብተው አደጋ ላይ የነበሩ ሦስት የቤተሰብ አባላት ለማንኛውም ብለው የድረሱልን መልዕክታቸውን በጠርሙስ ላይ ጽፈው ወደ ወንዝ ከተው ነበር።

በሚያስገርም ሁኔታ በጠርሙሱ ላይ የነበረውን መልዕክት ሰዎች አግኝተው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሕይወታቸውን መታደግ ችለዋል።

'የእሳተ ገሞራ ቱሪዝም'፡ አፍቃሬ እሳተ ገሞራዎች

ሰዓትን በትክክል የመቁጠር ጠቀሜታ

ከርቲስ ዊትሰን፣ የፍቅር ጓደኛውና የ13 ዓመት ልጃቸው ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ነበር ወደ ማዕከላዊ ካሊፎርኒያ ግዛት በመሄድ የቤተሰብ ጉዟቸውን የጀመሩት። እቅዳቸው ደግሞ አሮዮ ሴኮ የተባለውን ወንዝ በመከተል መጨረሻ ላይ የሚገኘውን ፏፏቴ መመልከት ነበር።

ልክ ፏፏቴው ጋር ሲደርሱም በገመድ ታግዘው በመውረድ እዛው አካባቢ ጊዜያዊ መጠለያቸውን ሠርተው ለመቆት ነበር ያሰቡት።

በሦስተኛው ቀን ግን ከትልልቅ ቋጥኞች ሥር መውጣት በማይችሉበት ሁኔታ እራሳቸውን አግኝተዋል። ቋጥኞቹ በሁለቱም በኩል 15 ሜትር ወደላይ ከፍታ ያላቸው ሲሆን፤ ይዘውት የነበረውም ገመድ ወደታች ለመውረድ እንጂ ወደላይ ለመውጣት የሚያገለግል አልነበረም።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፤ እነሱ የነበሩበትና በቋጥኞቹ መካከል ያለው ቦታ ከወንዙ በሚመጣ ውሃ መሞላት ጀመረ።

''ውሃው ከፍ እያለ ሲመጣና ምን አይነት አደጋ ውስጥ እንደገባን ስረዳ ልቤ ቀጥ ብላ ነበር'' ብሏል ከርቲስ ከሲኤንኤን ጋር ባደረገው ቆይታ።

የሠላም ተጓዧ ሉሲ (ድንቅነሽ) ምን ደረሰች?

ምንም አይነት የስልክ ኔትዎርክ በቦታው ስላልነበር የድረሱልን መልዕክት ማስተላለፍ እንኳን አቅቶት የቆየው ቤተሰብ በመጨረሻ ያለውን አማራጭ ለመጠቀም ወሰነ።

በእጃቸው ላይ የነበረውን ጠርሙስ በመፈቅፈቅ ''በፏፏቴው በኩል መውጣት አቅቶን ተይዘናል፤ እባካችሁ ድረሱልን'' የሚል መልእክት ጽፈው ወደ ወንዙ ወረወሩት።

Image copyright Cindi Barbour
አጭር የምስል መግለጫ መልዕክቱ የተጻፈበት ጠርሙስ

ጠርሙሱ ግማሽ ኪሎ ሜትር ያህል በወንዙ ላይ እየተንሳፈፈ ከተጓዘ በኋላ በአካባቢው ጉዞ እያደረጉ የነበሩ ሁለት ሰዎች ያገኙታል። ወዲያውም ጉዳዩን ለአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ያሳውቃሉ።

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችም ወዲያው ፍለጋቸውን የጀመሩ ሲሆን፤ እኩለ ሌሊት አካባቢ ሦስቱንም የቤተሰብ አባለት ከባድ የሚባል ጉዳት ሳይደርስባቸው አግኝተዋቸዋል።

ከርቲስ ዊትሰን እና ቤተሰቡ "ሕይወታችን በመትረፉ እጅግ ደስተኞች ነን። ሕይወታችንን ያተረፉት እነዛ ሁለት ተጓዦችን አግኝተን ማመስገን እንፈለጋለን" ብለዋል።