ለሥራ ከከተማ የወጣ ሰራተኛ ወሲብ ሲፈጽም በመሞቱ ቀጣሪው ኃላፊነቱን ይውሰድ ተብሏል

የወንድና ሴት ፎቶ Image copyright Getty Images

በአንድ የፈረንሳይ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረ ግለሰብ ለሥራ ከከተማ ወጣ በለበት አጋጣሚ ወሲብ ሲፈጽም ህይወቱ በማለፉ ድርጅቱ ተጠያቂ ይሆናል መባሉ እያነጋገረ ነው።

ሰውዬው ለድርጅቱ ሥራ በሄደበት ድንገት የልብ ድካም አጋጥሞት ስለሞተ ቤተሰቦቹ ከቀጣሪው ድርጅት ካሳ ማግኘት አለባቸው ሲል በፓሪስ የሚገኝ ፍርድ ቤት ብይን አስተላልፏል።

ህንዳዊቷ በ73 ዓመታቸው መንታ ተገላገሉ

እንግሊዛውያን የወሲብ ሕይወታቸው ''ደካማ ነው'' ተባለ

ድርጅቱ ደግሞ ሰውዬው ምንም እንኳን ለስራ ቢሆንም የሄደው፤ ህይወቱ ያለፈው ግን የድርጅቱን ሃላፊነት ሲወጣ ሳይሆን ባረፈበት ሆቴል ከምትገኝ ሌላ እንግዳ ክፍል ውስጥ ገብቶ የግብረስጋ ግንኙነት ሲፈጽም ባጋጠመው የልብ ድካም ስለሆነ ተጠያቂ መሆን የለብኝም ብሎ ተከራክሯል።

ነገር ግን በፈረንሳይ ህግ መሰረት አንድ ተቀጣሪ በስራ ጉዞ ወቅት ለሚያጋጥመው ማንኛውም አይነት አደጋም ሆነ መጉላላቶች ቀጣሪው ድርጅት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ መሆኑን የፍርድ ቤቱ ዳኛ ገልጸዋል።

ዣቪዬር የተባለው ግለሰብ በባቡር ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ 'ቲኤስኦ' በተባለ ድርጅት ውስጥ በማህንዲስነት ነበር ተቀጥሮ የሚሰራው።

የዣቪዬር ጤና መድህን አቅራቢ ድርጀት ደንበኛዬ በስራ ጉዞ ወቅት ባጋጠመው ድንገተኛ የጤና እክል ህይወቱ ስላለፈች ካሳውን ሊከፍል የሚገባው ቀጣሪው ድርጅት ነው በማለት ሲከራከር ነበር።

ለወሲብ ትክክለኛው ዕድሜ የቱ ነው?

ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል?

''ምናልባት የልብ ድካሙ ገላውን ሲታጠብ አልያም ለስራ ሲወጣ ሊያጋጥመው የችል ነበር። ማንኛውም ሰው የሚያደርገውን ነገር እያደረገ ነው ህይወቱ ያለፈው፤ ስለዚህ እንደተለየ ነገር መወሰድ የለበትም'' የሚል መከራከሪያ አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱም የሃገሪቱን ህግ እና የመከራከሪያ ነጥቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት ቲኤስኦ የተባለው ድርጅት ለሰራተኛው ሞት ካሳ እንዲከፍ የመጨረሻ ውሳኔውን አስተላልፏል።

ተያያዥ ርዕሶች