አውስትራሊያዊው ተናካሽ ቁራ ሲሸሽ ከብስክሌት ወድቆ ሞተ

ቁራ Image copyright Getty Images

የ76 ዓመቱ አውስትራሊያዊው ከተናካሽ ቁራ እራሱን ለማዳን ሲሸሽ ከብስክሌት ላይ ወድቆ ህይወቱ አለፈ።

ፖሊስ እንዳለው ብስክሌት ሲጋልብ የነበረው አዛውንት ከአደገኛው ወፍ ለማምለጥ ጥረት ሲያደርግ መንገድ ስቶ ከፓርክ አጥር ጋር ተጋጭቶ ህይወቱ አልፏል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ህይወቱን ለማዳን ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ጭንቅላቱ ላይ የደረሰበት ጉዳት ከባድ ስለነበር ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም።

'ኒከርስ' የማይሸጥ የማይለወጠው ቁመተ ሎጋው በሬ

የዓለማችን ለኑሮ ምቹ የሆኑ 10 ከተሞች እነማን ናቸው?

በአውስትራሊያ ጥቁር እና ነጭ ቀለም ያላቸው ቁራዎች በፍጥነት እየበረሩ በእግረኞች እና ብስክሌት በሚጋልቡ ሰዎች ላይ ጉዳት የማድረሳቸው ዜና የተለመደ ነው።

በፓርኩ አቅራቢያ በወፎቹ በርካታ ተመሳሳይ ጥቃቶች መድረሳቸውን የአከባቢው መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ባለሙያዎች እንደሚሉት አእዋፋቱ በመራቢያቸው ወቅት በአካባቢያቸው የሚገኝ ማንኛውንም እንስሳ ያጠቃሉ። ከፈረንጆቹ ሞቃታማ ወራት በኋላ በሚኖሩት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ደግሞ የአዋፋቱ ጥቃት ይጨምራል።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ከፈረንጆቹ ሞቃታማ ወራት በኋላ በሚኖሩት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የአዋፋቱ ጥቃት ይጨምራል።

ወደ ጫካነት የተቀየረው ስታዲየም

በሲድኒ ከተማ የሚገኝ የአንድ አካባቢ ምክር ቤት በሰዎች ላይ ጥቃት እያደረሱ የሚገኙ ቁራዎችን ለመግደል ውሳኔ ማስተላለፉ የብዙዎች መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።

የአውስትራሊያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እንደዘገበው ሌላ አንድ ነዋሪ ከቁራው ለመሸሸ ረዥም ሰዓት መሮጡን ተከትሎ ባጋጠመው የልብ ህመም ለሆስፒታል አልጋ ተዳርጓል።