1 ኪሎ ከ30 ሺህ ብር በላይ የሚሸጠው የዓለማችን ውዱ አይብ ከየትኛዋ እንስሳ የሚገኝ ይመስልዎታል?

ለአንድ ኪሎ ግራም የአህያ አይብ ከ30ሺህ ብር ይጠየቃሉ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ለአንድ ኪሎ ግራም የአህያ አይብ ከ30ሺህ ብር ይጠየቃሉ

''የተለየ ጣዕም አለው፣ የትኛውም ምግብ ውስጥ ቀምሰውት የማያውቁት አይነት ጣዕም ነው ያለው"

ይህን ያሉት የቀድሞ የሰርቢያ የሕዝብ እንደራሴ ከአህያ ወተት ስለሚሰራው አይብ ሲናገሩ ነው።

ሰርቢያዊው የቀድሞ የሕዝብ እንደራሴ ስሎቦዳን ሲሚክ ባልተለመደው መስክ ከአህያ ወተት አይብ ማምረት ጀምረዋል።

"ምን ልታዘዝ አልተቋረጠም" ፋና ብሮድካስቲንግ

ዋሾዎችን ለመለየት የሚረዱ መንገዶች

የምርቱ አቅርቦት አነስተኛ ስለሆነ ለአንድ ኪሎ ግራም የአህያ አይብ 1000 ዩሮ ይጠየቅበታል።

"የአህያ አይብን የምንሸጠው በ50 ግራም አስተኛ መጠን ነው። ይህም ለ10 ሰው የሚበቃ ነው'' ብለዋል ሰርቢያዊው ስሎቦዳን ሲሚክ።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ አይቡ በ50 ግራም ነው የሚሸጠው

ፍቅረኞቻቸውን ለማስደሰት የሚፈልጉ ወጣት ወንዶች በስጦታ መልክ ይህን አይብ እንደሚገዙ ስሎቦዳን ሲሚክ ይናገራሉ።

እውቁ ሰርቢያዊው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ኖቫክ ጆኮቪች በስሩ ለሚተዳደሩት ምግብ ቤቶች ይህን የአህያ አይብ በመግዛት ደንበኛ እንደሆነም ተነግሯል።

ስሎቦዳን ሲሚክ በዓመት ከአህያ ወተት የሚያመርቱት የአይብ መጠን 50 ኪሎ ግራም ብቻ መሆኑን በመጥቀስ፤ ወደ ሌሎች ሃገራት ለመላክ በወተት ውጤቶች ዙሪያ ያለው ጥብቅ ሕግ ችግር እንደሆነባቸው ተናግረዋል።

ራማፎሳ በሌሎች አፍሪካውያን ላይ በደረሰው ጥቃት ማፈራቸውን ገለፁ

''ይሁን እንጂ ቱጃሮች ሰርቢያ ድረስ እየመጡ ልዩ የሆነውን ምርቴን ይገዛሉ'' የሚሉት ስሎቦዳን ሲሚክ ከዚህ ቀደም ከማሌዢያ የመጣ አንድ ባለሃብት 15 ኪሎ ግራም የአህያ አይብ እንደገዟቸው ያስታውሳሉ።

ከአህያ ወተት የሚሰራው አይብ ለምን ተወደደ?

ሚስጢራዊ ቀመር።

በመላው ዓለም አህዮች ሰው እና ቁሳቁሶችን ከአንድ ወደ ሌላ ቦታ እንዲያንቀሳቅሱ ነው ጥቅም ላይ የሚውሉት።

በአንዳንድ ቦታዎች የአህያ ወተት ጥቅም ላይ ይውላል። ከወተቱ አይብ ማውጣት ግን አስቸጋሪ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ የአህያ ወተት ሴስቲን የተባለ ፕሮቲን በውስጡ ስለሌለ አይረጋም።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ስሎቦዳን ሲሚክ አህያ ሲያልቡ። ስሎቦዳን ከአህያ የሚሰራው አይብ ለጤና እጅግ ጠቃሚ ነው ይላሉ

ስለዚህም ስሎቦዳን ሲሚክ ይህን ለመቅረፍ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ባለሙያ በመቅጠር መፍትሄ አበጁለት- ይህ ቀመር ትልቅ ሚስጥር ነው።

"ባለሙያው ብቻ ነው የሚያውቀው- እኔ ራሱ ምን እንደሆነ አላውቅም" ይላሉ ስሎቦዳን ሲሚክ።

አህዮች ከላሞች ያነሰ የወተት ምርት ነው የሚሰጡት። አንድ ኪሎ አይብ ለማምረት 25 ሊትር ወተት ያስፈልጋል ይላሉ።

ስሎቦዳን ሲሚክ በዚህ የተለየ መስክ የተሰማሩት ሃብት ለማካበት ሳይሆን ፍላጎቱ ስላደረብኝ ነው በማለት ያስረዳሉ።

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ የአህያ ወተት ሴስቲን የተባለ ፕሮቲን በውስጡ ስለሌለው አይረጋም

ኑሯቸውን ከሰርቢያ መዲና ቤልግሬድ 80 ኪሎ ሜትር ላይ የመሰረቱት የቀድሞ የሕዝብ እንደራሴ፤ ከአህያ በስተቀር ሁሉም አይነት ሊባል በሚችል የቤት እንስሳቶች ነበሯቸው።

"አህያ ለምን አይኖረኝም?'' ሲሉ ራሳቸውን ጠያቁ።

ከዚያም 20 አህዮችን ገዙ።

"በሰርቢያ አህያ ጅል የሆነ እንስሳ ተደርጎ ይታሰባል። ይህ ግን እጅጉን የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው። አህያ ምርጥ የሆነ እንስሳ ነው" በማለት ስሜታዊ ሆነው ይናገራሉ።

ከዚያም አህያ እያለቡ ወተቱን መሸጥ ጀመሩ።

ከነፍስ የተጠለሉ የዘሪቱ ከበደ ዜማዎች

ወተቱን በመሸጥ የሚያገኙት ገቢ አነስተኛ በመሆኑ፤ ከወተቱ አይብ የማምረቱ ሃሳብ ተግባራዊ አደረጉ።

"በየቀኑ የአህያ ወተት እጠጣለሁ። 65 ዓመቴ ነው። ምንም አይነት የጤና እክል የለብኝም"

ስሎቦዳን ሲሚክ በዘርፉ ላይ ውጤታማ መሆናቸውን ተከትሎ የእርሳቸውን ፈለግ በመከተል ሌሎች 10 ሰዎች ዘርፉን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።

"በሁሉም ዓለም የሚኖሩ ሰዎች የአህያን ወተት እንዲጠቀሙ እመክራለሁ" ብለዋል የቀድሞ የሕዝብ እንደራሴ።