ልጆቿን ወደ ትምህርት ቤት በማድረስ ላይ ሳለች የተገደለችው እናት

የስፔን ፖሊስ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ እናት ልጆቿን በመኪና ወደ ትምህርት ቤት እያደረሰች ነበር ይህ አሰቃቂ አደጋ የደረሰባት

ስፔናዊያን ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የከተተ ዜና ነው።

የ45 ዓመቱ ጎልማሳ የቀድሞ ባለቤቱን የገደለበት መንገድ ነው በአገሪቱ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረው።

ሰኞ ጠዋት እናት ልጆቿን አለባብሳ፥ ቁርስ አብልታ፣ በመኪና ወደ ትምህርት ቤት እየወሰደቻቸው ሳለ የቀድሞ ባለቤቷ መሣሪያውን አቀባብሎ ልጆቿ ፊት እዚያው መኪና ውስጥ ገድሏታል።

ጆሴ ሉዊስ ድርጊቱን ስለመፈጸሙም ለፖሊስ ተናዟል።

ቄሮ፣ ሴታዊት፣ ፋኖ…የትውልዱ ድምጾች

የተነጠቀ ልጅነት

ፖሊስ እንደሚለው ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በወንጀለኝነት አይታወቅም። የጾታ ጥቃት ክስ ቀርቦበትም አያውቅም።

ገዳይና ሟች (ባልና ሚስት) ፍቺ የፈጸሙት ባለፈው ዓመት ነበር።

Image copyright EUROPA PRESS NEWS

ሆኖም ገዳይ በቅርብ ጊዜ በፌስቡክ ገጹ ላይ "ትዳራችንን አፈረስሽ፤ አሁን ደግሞ ልጆቼን እንዳላያቸው ታደርጊያለሽ?" ሲል ጽፎ ነበር ብሏል አንድ የስፔን ጋዜጣ።

የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ግድያውን "ዘግናኝ"ሲሉ ያወገዙት ሲሆን ድርጊቱ ጸታዊ ጥቃት ነው እንፋለመዋለን ብለዋል በትዊተር ገጻቸው። "የሴቶች በየሥፍራው መገደል እስኪቆም ድረስ ትግላችን አይቆምም" ብለዋል።

ይህ የወንጀል ድርጊት የተፈጸመው በጋሊሺያ ክልል ቫልጋ በተባለች ከተማ ውስጥ ነው።

"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ"

የተደፈረችው የ3 ዓመት ህፃን በአስጊ ሁኔታ ትገኛለች

የልጆቹ እናት መኪና ውስጥ ልጆቿ ፊት ከመገደሏ በፊት ድረሱልኝ ስትል የጠራቻቸው እህትና እናቷንም ግለሰቡ ተኩሶ ገድሏቸዋል።

ሦስቱን የቤተሰብ አባላትን ልጆቹ ፊት ከገደለ በኋላ ሽጉጡን በአቅራቢያ ወንዝ ወርውሮ ለአፍታ ተሰውሮ ነበር ግለሰቡ። በኋላ ነው በራሱ ጊዜ እኔ ነኝ ሲል ለፖሊስ እጁን የተሰጠው።

የቫልጋ ከተማና አካባቢው ይህ አሰቃቂ ወንጀል ተከትሎ የሦስት ቀን ሐዘን አውጀዋል። የአራትና የሰባት አመቱ አዳጊዎች አጎታቸው ጋ ጥበቃ እየተደረገላቸው በልዪ ከለላ ላይ ይገኛሉ።

ተያያዥ ርዕሶች