የኤርትራ ወጣቶችና ምኞታቸው

አሥመራ በተካሄደው ፌስቲቫል ላይ የባህል ጨፈራቸውን የሚያሳዩ ኤርትራውያን ወጣቶች
አጭር የምስል መግለጫ አሥመራ በተካሄደው ፌስቲቫል ላይ የባህል ጨፈራቸውን የሚያሳዩ ኤርትራውያን ወጣቶች

ከሶስት ሳምንታት በፊት ቢቢሲ በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን ከ15 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድርን ለመዘገብ ፍቃድ አግኝቶ ወደ አሥመራ አቅንቶ ነበር።

በኤርትራ በነበርን ቆይታ ያየነውን እና የሰማነውን በሶስት ክፍሎች አሰናድተናል። ሶስተኛው ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል። ሁለተኛውን ክፍል ለማንበበ ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

ማሳሰቢያ፡ በኤርትራ በነበረን ቆይታ የዘገባ ርዕሶቻችን እና እንቅስቃሴዎቻችን የተገደቡ ነበሩ።

በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት እንደ የጎሮጎሲያኑ የቀን አቆጣጠር ነው።

የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች


አጭር የምስል መግለጫ አንድ በዕድሜ የገፉ አባት በአሥመራ ከተማ ከፑሽኪን ሃውልት ስር ተቀምጠው

እግርዎ አሥመራ እንደረገጠ ቀድመው ሊያስተውሉ ከሚችሏቸው መካከል አንዱ፤ አሥመራ አዛውንት የሚበዛባት እና ወጣት ብዙም የማይታይባት ከተማ ስለመሆኗ ነው።

አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ

የአሥመራን ጎዳናዎች በፎቶ

የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ከጠቅላለው ህዝብ እድሜያቸው ከ35 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶች ቁጥር ከ65 በመቶ ይሆናል ይላል። ይህ ግን ለኤርትራ የሚሰራ አይመስልም። ግራ ቀኞችን ቢያማትሩ በብዛት የሚመለከቱት እድሜያቸው ጠና ያለ አዛውንቶችን ነው። 'ወጣቱ ወዴት አለ?' ብለው ራስዎትን መጠየቅዎ አይቀርም።

እያደጉ ባሉ የአፍሪካ ሃገራት ወጣቱ ትውልድ የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ሃገሩን ጥሎ የመሸሹ ዜና የተለመደ ሆኗል። 2016 ላይ የወጣ አንድ ሪፖርት እንደሚጠቁመው ከአፍሪካ ሃገራቸውን ጥለው ከሚወጡ ወጣት አፍሪካውያኖች አብዛኛዎቹ ኤርትራውያን ናቸው።

የአፍሪካ ቀንድ ሃገራት ወጣቶች የተሻለን ህይወት ፍለጋ ሃገር ጥለው እንደሚሰደዱ አደባባይ የሚያውቀው ሃቅ ነው። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ በድንበር በኩል ሃገር ጥለው የሚወጡ ወጣቶች ቁጥር እጅጉን ማሻቀቡን ነዋሪዎች ነግረውናል። ሆኖም፤ በዚህ ያክል መጠን ከተማዋ ወጣት አልባ መሆኗ የሚያስደንቅ ነው።

አጭር የምስል መግለጫ በአሥመራ 'ERITREA' ወይም 'Proud Eritrean' [ኩሩ ኤርትራዊ] ተብሎ የተጻፈባቸው ከነቴራ ለብሰው የሚታዩ ወጣቶች ብዙ ናቸው።

ይህ እና ሌሎች ምክንያቶች ተደማምረው አሥመራን "አድማ ላይ ያለች ከተማ" አስመስለዋታል። አንድ ከተማ አድማ ላይ ስትሆን በራቸውን የሚዘጉ የንግድ ተቋማት ብዙ ናቸው። መንገድ ላይ የሚታዩ የተሽከርካሪዎች ቁጥር አነስተኛ ነው። በአሥመራም ያስተዋልነው እንዲሁ ነው። ብዙ የንግድ እንቅስቃሴ አይታይም። የትራፊክ ፍሰቱ ቀሰስተኛ ነው።

ፓስፖርት የለም

አንድ ኤርትራዊ ፓስፖርት ማግኘት የሚችለው የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠለትን ብሔራዊ አገልግሎት አጠናቆ ከመንግሥት አካል ፓስፖርት ለማግኘት ይሁንታን ሲያገኝ ነው።

በእነዚህ መስፈርቶች ምክንያት ወጣቶች ፓስፖርት የማግኘት እድላቸው እጅግ አነስተኛ ነው።

የዛሬዋን ኤርትራ የሚገልጹ አስደናቂ እውነታዎች

በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል

''ፓስፖርት ማግኘት የማይታሰብ ነገር ነው" ይላል በአንድ ምሽት ለእራት አብሮን ያመሸ ወጣት። "ብሄራዊ አገልግሎት ጨርሰህ፣ ከመንግሥት ቢሮ ደብዳቤ ተጽፎልህ ፓስፖርት ስታገኝ የ40 ወይም የ45 ዓመት ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ትሆናለህ" ይላል።

ከሁነኛ የመረጃ ምንጮች እንደሰማነው በቁጥር ቀላል የማይባሉ ኤርትራውያን ወጣቶች ድንበር በማቋረጥ ወደ ኢትዮጰያ ከተሻገሩ በኋላ ኢትዮጵያዊ ነን በማለት ፓስፖርት ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ ፊታቸውን እያዞሩ ነው።

ቋንቋ

ትግርኛ እና አረብኛ የኤርትራ የሥራ ቋንቋዎች ሲሆኑ፤ በአሥመራ እንግሊዘኛ በስፋት ይነገራል። በእድሜ ገፋ ያሉት ካልሆኑ በቀር ወጣቶች አማርኛ መናገር ይከብዳቸዋል። ትግርኛ የማይችሉ ከሆነ በእንግሊዘኛ ነው ሊግባቡ የሚችሉት። ብዙዎቹ ወጣቶቹ ባማረ ዘዬ እንግሊዘኛ ጥሩ አድርገው መናገራቸው ግርምትን ፈጥሮብናል። በአሥመራ ከተማ ብዙ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ቤት መኖሩ ለዚሁ ሳይጠቅማቸው አልቀረም።

የቅኝ ገዢው ጣሊያን ብዙ አሻራ ያረፈባት አሥመራ፤ በቋንቋ ረገድ ግን ጣሊያንኛን የሚያወሩ ሰዎች አላጋጠሙንም። በእድሜ ገፋ ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ግን ጣሊያንኛ እንደሚያወሩ ሰምተናል።

ዘናጮቹ የአሥመራ ልጆች

የአሥመራ ወጣቶች በተለይ እንስቶቹ የለበሱትን ከሚጫሙት ጫማ ጋር አዋህደው ሽር ይላሉ። የልብስ መሸጫ ቡቲኮች አይታዩም። በአሥመራ የሚገኙ ቡቲኮችን ቆጥረው ሊጨርሱ ይችላሉ። ይህ ማጋነን አይደለም። ታዲያ እንዲህ የሚዘንጡት ወጣቶች የሚለብሱትን ልብስ፤ የሚጫሙትን ጫማ ከየት እየገዙት ነው? ብልን አንድ የታክሲ ሹፌርን ጠየቅነው ''ባህር ማዶ ዘመድ የሌለው የለም፤ ልብስ ይላካል'' ሲል መለሰልን።

ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ

አሥመራ ያሉ ቡና ቤቶች ከሰኞ እስከ ሐሙስ የሚሰሩት እስከ እኩለ ለሊት ብቻ ነው። የምሽት ክበቦችም ቢሆኑ በዚሁ ቀጭን ትዕዛዝ ስር የወደቁ ናቸው። ከአርብ እስከ እሁድ ድረስ ግን ይህ ገደብ የለም።

በአሥመራ የመንገድ ላይ የወሲብ ንግድ ፈጽሞ የተከለከለ ነው። ስድስት ወራት ያሳስራል።

አጭር የምስል መግለጫ ከ15 ዓመት በታች የኤርትራ ብሔራዊ ቡድንን ለመደገፍ ከስታዲየም የተገኙ ደጋፊዎች።

ስፖርት

በብስክሌት ግልቢያ የሚታወቁት ኤርትራውያን ለእግር ኳስ ጥልቅ ፍቅር እንዳላቸው ታዝበናል። አሥመራ እግር ኳስ በስሜት የሚታይባት ከተማ ነች። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ደግሞ ተወዳጁ ሊግ ነው።

ጥንት ፊልም እና ቲያትር ይታይባቸው የነበሩት የአሥመራ ሲኒማ ቤቶች፤ ዛሬ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የሚናፍቁ ኳስ ወዳጆች ይታደሙበታል።

የአርሰናል እና ማንችስተር ደጋፊዎች በብዛት ያሉባት ከተማ ናት አሥመራ።

የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጦርነት ሲታወስ

አንዱ የአርሰናል ደጋፊ ''ቼልሲን የሚደግፉት ከቆላ የሚመጡት ናቸው" ብሎ ከተሳለቀ በኋላ፤ "ፕሬዝደንቱ ራሱ የአርሰናል ደጋፊ ናቸው'' በማለት በልበ ሙሉነት ይናገራል።

ብሔራዊ አገልግሎት

ብሔራዊ አገልግሎት የተጀመረው 1994 ላይ ሲሆን የኤርትራ መንግሥት 'ኤርትራ የወረራ ስጋት ያለባት ሃገር ናት' በማለት ወጣቶችን በየዓመቱ ሳዋ ተብሎ ወደሚጠራው ካምፕ እየወሰደ ወታደራዊ ስልጠና ይሰጣል።

"ታዳጊዎችን ማብቂያ ለሌለው ባርነት እየተዳረጉ ነው" የሚል ክስ በተደጋጋሚ የሚቀርብበት የኤርትራ መንግሥት፤ ከኢትዮጵያ ጋር የሰላም ስምምነት ከተደረሰም በኋላ ብሔራዊ አገልግሎቱን እንዳስቀጠለ ነው።

በሳዋ ማሰልጠኛ ማዕከል ማስተማር የነበረበትና ባለፈው ዓመት ኤርትራን ጥሎ የተሰደደው የ25 ዓመቱ ወጣት ለሂማን ራይትስ ዋች "የፊዚክስ ትምህርትን ለማስተማር ከተመለመልክ፤ እድሜ ልክህን የፊዚክስ መምህር ሆነህ ትቀራለህ" ሲል ተናግሯል።

Image copyright EDUARDO SOTERAS

ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ማናቸው?

ፕሬዝደንት ኢሳያስ ስለ ግል ህይወታቸው በአደባባይ አይናገሩም። ስለ እርሳቸው የሚያውቁት ጥቂቶች ናቸው።

1936 ላይ በአሥመራ የተወለዱት ኢሳያስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው በከፍተኛ ውጤት ማጠናቀቅ በመቻላቸው፤ በቀድሞ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ገብተው የምህንድስና ትምህርት እንዲከታተሉ የሚያስችላቸው ቢሆንም ትምህርታቸውን አቋርጠው የኤርትራ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባርን ለመቀላቀል ወደ ሱዳን አቀኑ።

ፕሬዝደንት ኢሳያስ ታጋይ ከነበሩት ሳባ ኃይሌ ጋር ትዳር መስረተው በአሁኑ ወቅት የሁለት ወንዶች እና የአንዲት ሴት አባት ናቸወ።

በ1962 ዓ.ም የኤርትራ ነጻነት ግንባር ውስጡ በተፈጠረ አለመስማማት በሦስት ተከፈለ። ከ10 ያልበለጡ አባላት የነበሩት የኢሳያስ አፈወርቁ ቡድን ወደ ደቡባዊ ምሥራቁ ኤርትራ በመሄድ ትግሉን ጀመረ።

የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ?

የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ጦስ በሶማሊያ?

ከአንድ ዓመት በኋላ ኢሳያስ የብሄር እና የኃይማኖት ልዩነቶችን ለማጥበብ እና የተቀናጀ ትግልን ስለማካሄድ የሚያትት "ትግላችን እና ግቡ" የተሰኘ ማኒፌስቶ ጽፈው ነበር።

1979 ላይ የግንባሩ ሊቀመንበር ተደርገው የተመረጡት ኢሳያስ፤ 1985 ላይ የተደረገውን ህዝበ ውሳኔ ተከትሎ የኤርትራ የመጀመሪያው ፕሬዝደንት እና የብሔራዊ ምክር ቤቱ ዋና ጸሐፊ ተደረገው ተመረጡ።

በቁመተ ረዥሙ ብቻም ሳይሆን ለረዥም ዓመታት ሃገር ያስተዳደሩም መሪ ለመሆን የበቁት ፕሬዝደንት ኢሳያስ የመንግሥት የሥራ አስፈጻሚን እና የፍትህ አካሉን በቁጥጥራቸው ስር እንዲሆን አድርገዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ