ሳራህ ቶማስ፡ ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ ያለማቋረጥ የዋኘችው የጡት ካንሰር ታማሚ

ሳራህ ቶማስ ስትዋኝ Image copyright SARAH THOMAS
አጭር የምስል መግለጫ ሳራህ ቶማስ

የጡት ካንሰር የሕክምና ክትትሏን ባለፈው ዓመት ያጠናቀቀችው ሳራህ ቶማስ፤ የእንግሊዝን የውሃ ሰርጥ ያለምንም እረፍት አራት ጊዜ በዋና ያቋረጠች የመጀመሪያዋ ሴት ሆናለች። 'ኢንግሊሽ ቻነል' የአትላንቲክ ውቅያኖስ አነስተኛ ክፍል ሲሆን፤ ደቡባዊ እንግሊዝን ከሰሜን ፈረንሳይ ጋር የሚለያይ የውሃ አካል ነው።

የኦሎምፒክ ተወዳዳሪው በመስጠም ላይ የነበረን ሙሽራ ታደገ

የባርሳ ሴቶች ከወገብ በላይ ራቁት ለመሆን ድምጽ ሰጡ

የ37 ዓመቷ ሳራህ ይህን እልህ አስጨራሽ የሆነ ውድድር ያደረገችው ባሳለፍነው እሁድ ሲሆን ለ54 ሰዓታትን ከዋኘች በኋላ ልታጠናቅቅ ችላለች።

ሳራህ የጡት ካንሰር ሕክምናዋን ያጠናቀቀችው ባለፈው ዓመት ሲሆን፤ ይህንን ገድሏን "እንደ እኔ ከሞት ለተረፉት መታሰቢያ ይሁን" ብላች።

ዋናው 128.7 ኪሎ ሜትር (በ80 ማይል) የሚያስጉዝ ቢሆንም ሳራህ ባጋጠማት ከፍተኛ ማዕበል ምክንያት 209.2 ኪሎ ሜትር (130 ማይል) ርቀት ለማዋኘት ተገዳለች።

የአሜሪካ ኮሎራዶዋ ሳራህ፤ ዋናዋን ያጠናቀቀችው ባሳለፍነው ማክሰኞ ነበር።

የማራቶን ዋናተኛዋ "በድል ማጠናቀቄን በፍፁም ማመን አልቻልኩም፤ በጣም ደስ ብሎኛል" ስትል ዋናውን አጠናቅቃ በዶቨር የባህር ዳርቻ ላይ እንዳረፈች ለቢቢሲ ተናግራለች።

"በጣም በርካታ ሰዎች እኔን ለማግኘትና መልካም ለመመኘት በውሃው ዳርቻ ላይ ተገኝተው ነበር። እነርሱ በጣም ደስ ብሏቸዋል፤ እኔ ግን ባለማመን ደንግጬ ነበር" ብላለች ሳራህ።

ሰውነቷ በድካም እንደዛለ የተናገረችዋ ሳራህ ለቀናት መተኛት እንደምትፈልግም ገልፃለች።

የሳራህን ገድል አስመልክቶም ዋናተኛው ለዊስ ፐግህ በትዊተር ገፁ ላይ "የሰውን ልጅ የአቅም ልክ አሳይተናል ስንል፤ አንዳንዶች ያንን ክብረ ወሰን ይበጣጥሱታል" ሲል አሞካሽቷታል። እንኳን ደስ ያለሽ ሲልም መልካም ምኞቱን ገልጾላታል።

የሳራህ እናት ቤኪ ባክስተር በበኩላቸው፤ "በሕይወት ጉዞዎቿ ሁሉ አብሬያት አለሁ፤ የአሁኑ ግን እጅግ አስፈሪው ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ልጃቸው የተፈጥሮ አድናቂ ብትሆንም በዚሀ ጉዞዋ በርካታ ተግዳሮቶችና የሆድ ህመም እንዳጋጠማት አልሸሸጉም።

ባለፈው ዓመት የጡት ካንሰር ሕክምናዋን ያጠናቀቀችው ሳራህ፤ መዋኘትን እንደ አንድ ሕክምና አድርጋ ትጠቀምበት ነበር።

የሳራህ ደጋፊ ቡድን አባል የሆነችው ኤሌን ሆውሌይም፤ "የጓደኛየ ስኬት እጅግ አስደናቂ፣ ያልታሰበ እና የተለየ ነው" ስትል ገልጻዋለች።

የዋና ማራቶንን ድንበር ያለፈች ብላታለች።

ማራቶን ለማዋኘት ምን አነሳሳት?

የዋና ልምድ ያላት ሳራህ በውሃ ላይ የምታደርገውን ዝግጅት ያጠናቀቀችው በአውሮፓዊያኑ 2007 ነበር። የእንግሊዙን 'ቻነል'ን በዋና ለመጀመሪያ ጊዜ ያቋረጠችው በ2012 ሲሆን፤ በድጋሚ በ2016 በዋና አቋርጠዋለች።

የጡት ካንሰር የያዛት የጡት ካንሰር ሀኪም

"ዛሚ አልተሸጠም፤ በትብብር እየሠራን ነው" ጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱ

ለፊልም ሠሪው ጆን ዋሸር፤ "32 ኪሎ ሜትር (20 ማይል) ርቀት ስዋኝ፤ ከዚህ በላይ መዋኘት እንደምችል ይሰማኝ ነበር፤ በመሆኑም ምን ያህል ልጓዝ እንደምችል ማየት ፈለግኩ" ስትል የተነሳሳችበትን ምክንያት አስረድተዋለች።

ከዚያም በ2017 ነሐሴ ወር ላይ በአሜሪካና በካናዳ ድንበር በሚገኘው ቻምፕሌን ሐይቅ 168.3 ኪሎ ሜትር (104.6 ማይል) ዋኘች። ከዚያ በኋላ ነበር የጡት ካንሰር ሕመም አጋጥሟት ሕክምና መከታተል ጀመረች።

ሳራህ የጡት ካንሰር ሕክምናዋን ባለፈው ዓመት ነበር ያጠናቀቀችው። አሁን የእንግሊዙን 'ቻነል' በመዋኘት የሰበረችውን ክብረ ወሰን፤ ለሌሎች ከሞት ለተረፉት የእሷ ቢጤ ታማሚዎች መታሰቢያ ይሁንልኝ ብላለች።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ