'ሶሪያውያን' ስደተኞች የስፖርት ቡድን አባላት በመምሰል ድንበር ሲሻገሩ ግሪክ ውስጥ ተያዙ

ስደተኞቹ ሶሪያውያን ሳይሆኑ አይቀርም ተብሏል። Image copyright Police handout
አጭር የምስል መግለጫ ስደተኞቹ ሶሪያውያን ሳይሆኑ አይቀርም ተብሏል።

የሶሪያ ዜጎች ሳይሆኑ እንዳልቀረ የተገመቱ 10 ሰደተኞች የመረብ ኳስ ተጫዋች መስለው ወደ ስዊዘርላንድ በሕገ-ወጥ መንገድ ለመጓዝ ሲሞክሩ በግሪክ ፖሊስ አቴንስ አየር ማረፊያ ውስጥ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

የቡድኑ አባላት ተመሳሳይ የስፖርት ትጥቅ የለበሱ ሲሆን ሁለት የመረብ ኳሶችም በእጆቻቸው ይዘው ነበር።

ፖሊስ እንደሚለው ሶሪያውያን እንደሆኑ የተገመቱት 10ሩ ስደተኞች የእራሳቸው ባልሆነ ፓስፖርት ለመጓዝ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።

ሚሊዮን ዶላር አጭበርባሪው ስደተኛ

«ሳሸንፍ ጀርመናዊ ስሸነፍ ስደተኛ» ኦዚል

ካለሁበት፡ ''በሜዲትራንያን ባህር ከመስመጥ መትረፌ ሁሌም ይደንቀኛል"

ስደተኞቹ መዳረሻቸውን ወደ የስዊዘርላንዷ ዙሪክ ማድረግ ነበር ህልማቸው።

ግሪክ ወደ ተቀሩት የአውሮፓ ሃገራት መሄድ ለሚፈልጉ ስደተኞች ቅድሚያ መሻገሪያ ሃገር ናት።

ሌስቦስ እና ሳሞስ የሚባሉ ታዋቂ የግሪክ ደሴቶችን ጨምሮ ብዙ ደሴቶች ከአቅማቸው በላይ ስደተኞችን በማስተናገዳቸው ማህብራዊ ቀውስ እየተፈጠረባቸው ነው።

ተያያዥ ርዕሶች