ጣልያናዊው በአደን ወቅት በስህተት አባቱን ተኩሶ ገደለ

አሳማ Image copyright Getty Images

ጣልያን ውስጥ የዱር አሳማ ለማደን በወጡበት አባቱን ተኩሶ የገደለው ልጅ ክስ እንደተመሰረተበት ፖሊስ አስታወቀ።

የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በደቡባዊ ሳሌርኖ ግዛት በምትገኘው ፖሰቲግዮን ከተማ ክስተቱ ያጋጠመው አባትና ልጅ የዱር አሳማ ለማደን ጥቅጥቅ ባሉ ተክሎች መካከል በመጓዝ ላይ ሳሉ ነበር።

ጣልያን በተሸነፈችበት አድዋ ቆንስላዋን ለምን ከፈተች?

ጀብድ የፈጸመው ተማሪ ጣልያናዊ ዜግነት ሊሰጠው ነው

የ34 ዓመቱ ጣልያናዊ ለአደን በተጠንቀቅ ተዘጋጅቶ በነበረበት ወቅት ድንገት የሆነ ነገር ጥላ ሲመለከት ሳያቅማማ ተኩስ እንደከፈተ አምኗል። ተኩሶ የመታው ግን የገዛ አባቱን መሆኑን ሲገነዘብ ወዲያው ጉዳዩን ለፖሊስ በማሳወቅ አባቱ ቶሎ ህክምና እንዲያገኙ ጥረት አድርጓል።

ሟች የ55 ዓመቱ ማርቲኖ ጋዲዮሶ ወደ ሆስፒታል ቢወሰዱም ህይወታቸውን ማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል።

አባትና ልጅ የዱር አሳማ ለማደን ሲንቀሳቀሱበት የነበረው አካባቢ በብሔራዊ ፓርክነት ታጥሮ የነበረና አደን በፍጹም የተከለከለበት ነበር ተብሏል። ፖሊስም የሁለቱንም ግለሰቦች መሳሪያ በቁጥጥር ማዋሉን አስታውቋል።

ከአደጋው በኋላ በጣልያን የእንስሳትና አካባቢ መከላከያ ሊግ ፕሬዝዳንት ''ጣልያን ህግ አልባ እየሆነች ነው'' ሲሉ ተደምጠዋል።

ሳባ አንግላና፡ "ኢትዮጵያዊትም፣ ጣሊያናዊትም ሶማሊያዊትም ነኝ"

ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ አንድ 18 ዓመት ወጣጥ በአደን ወቅት በተመሳሳይ ሁኔታ ከተገደለ በኋላ የጣልያኑ የአካባቢ ሚኒስትር ሰርጂዮ ኮስታ ዘወትር እሁድ የሚደረጉ አደኖች መታገድ እንዳለባቸው አሳስበው ነበር።

በዛው ወር መጨረሻ ደግሞ አንድ 50 ዓመት ጎልማሳ እና የ20 ዓመት ወጣት አደን ላይ እያሉ በስህተት በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል።

ተያያዥ ርዕሶች