የኬንያዋ ጭርንቁስ ሰፈር የዓለም 'የድሀ ድሀ' ጉባኤን ልታዘጋጅ ነው

ኪቢራ Image copyright Getty Images

በኬንያ ዋና መዲና ናይሮቢ ያጡና የነጡ ዜጎች ተደጋግፈው የሚኖሩበት ሰፈር አለ፤ ኪቢራ የሚባል። ይህ ጭርንቁስ ሰፈር የዓለም የድህነት ጉባኤን ለማስተናገድ ተመርጧል።

ይህ ጉባኤ በአንዳንዶች "Davos with The Poor" ወይም "የድሆቹ ዳቮስ" የሚል ቅጽል ተሰጥቶታል።

በኒውዮርክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን በሚካሄዱ ስብሰባዎች ነው ኪቢራ ይህንን የጭርንቁሶች ጉባኤን እንድታስተናግድ መመረጧ የተገለጸው።

ይህንን ጉባኤ ከሚያሰናዱት አንዱ የሆነው ኬኔዲ ኦዴዴ እንደተናገረው የኬንያዋ ኪቢራ የተመረጠችው ድሆች ከሚኖሩባቸው ሰፈሮችና ከነዋሪዎቻቸው ብዙ ልንሰማና ልንማር ስለሚገባን ነው ብሏል።

ኢንተርኔት በሚቋረጥበት አገር የኢንተርኔት ነፃነት ጉባኤ?

የተቆጡት ቻይናዊ አከራይ የተከራያቸውን ገመና አጋለጡ

ኦዴዴ ጨምሮ ለቢቢሲ እንደተናገው ኑሮን ለማሸነፍ ከሚተጋው ሕዝብ መሀል ጉባኤው መዘጋጀቱ ልንለውጣቸው ስለምናስባቸው ነገሮች ቅርብ እንድንሆን ያግዘናል ይላል።

በዚህ የድሀ ድሀ ጉባኤ ንግግር የሚያደርጉት ሰዎች የሚመጡትም በመላው ዓለም እጅግ ከነጣ ድህነት የመጡ የጭርንቁስ ሰፈር ነዋሪዎች የሚወከሉ ዜጎች ይሆናሉ።

"እጅግ የናጠጡ የዓለም አገራት መሪዎች ከሚሰበሰቡበት የስዊዘርላንድ ዳቮስ ስብሰባ የሚለየውም ይኸው ነው። መሪዎች ሳይሆኑ ነዋሪዎች መድረኩን ስለሚያገኙት ነው" ይላል ኦዴዴ።

በዚህ ጉባኤ በዋናነት ከድሀው ማሕበረሰብ የተወጣጡ መሪዎች ይወከላሉ፤ አካባቢያቸውን እንዴት መለወጥ እንደሚፈልጉና እያደረጉ ያሉትንም ጥረት ይነግሩናል። ያ ነው ትምህርት የሚሰጠን ብሏል ከአዘጋጆቹ አንዱ የሆነው ኬኔዲ ኦዴዴ ።

ኦዴዴ በመጨረሻ እንዲሀ አለ፣ ለቢቢሲ፤ "ብዙውን ጊዜ ድህነትን ለመቅረፍ በሚል ሰዎች በአውሮፕላን ይበራሉ ወደ ሎንዶን፣ ወደ ኒውዮርክ። በውድ ቦታ ተሰብስበው የሚያወሩት ግን ስለ ኪቢራና መሰል ጭርንቁስ ሰፈሮች ነው።»

ተያያዥ ርዕሶች