ሁለት ሜትር ከሃያ አምስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ሴኔጋላዊ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች

ሁለት ሜትር ከሃያ አምስት ሳንቲሜትር ርዝማኔ ያለው ታኮ Image copyright Getty Images

ሴኔጋላዊው ታኮ ፎል ወደ ቅርጫት ኳሱ ዓለም የተቀላቀለው ገና ከሰባት ዓመታት በፊት ቢሆንም የ2.25 ሜትር ርዝማኔ ያለው ይህ ተጫዋች በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ (ኤንቢኤ) ከፍተኛ ስፍራ እያገኘ ነው።

ከዓለም ረዥሙ የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ሮማኒያዊው ጆርጅ ሙሬሳን በ6.3 ሴንቲ ሜትር የሚያጥረው የ23 አመቱ ታኮ፤ የታዋቂው የቦስተን ሴልቲክስ ከቋሚዎቹ አስራ አምስት ተጫዋቾች አንዱ ለመሆንም ጥረት ላይ ነው።

የደቡብ አፍሪካ ባሕር ጠላቂዎች በኬንያ አስክሬን ፍለጋ ላይ ሊሰማሩ ነው

የካቶሊክ ቄሶች ማግባት ይፈቀድላቸው ይሆን?

በአሜሪካዊቷ ፖሊስ የፍርድ ሂደት ምስክርነት የሰጠው የዐይን እማኝ ተገደለ

ሴልቲክስ ታኮ ፎልን የመረጠበት ምክንያትም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቡ እንደሆነም ተገልጿል።

በሴኔጋሏ መዲና ዳካር የተወለደው ታኮ፤ ወደ አሜሪካ የሄደው በ16 ዓመቱ ሲሆን፤ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ቅርጫት ኳስ ይጫወት ነበር።

ታኮ ለቢቢሲ እንደተናገረው፤ ዩኒቨርስቲው ውስጥ ብዙዎች ሙያውን እንዲያሳድግ ድጋፍ አድርገውለታል።

ታዳጊ ሳለ ብዙም ስለ ቅርጫት ኳስ እንደማያውቅ ይናገራል። ጊዜውን ያሳልፍ የነበረው ካርቱን ፊልሞች በማየት ነበር። የአያቱ ቅርጫት ኳስ መውደድ ስፖርቱ ላይ ፍቅር እንዲያሳድር አድርጎታል።

Image copyright Getty Images

ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ሙሉ ትኩረቱን ወደ ቅርጫት ኳስ አድርጓል። ጉዞው ግን አልጋ በአልጋ አልነበረም።

"ቅርጫት ኳስ መጫወት አልችልም ነበር። ብዙ ነገር መማር ይጠበቅብኝ ነበር። እድለኛ ሆኜ ብዙ ሰዎች ራሴን እንዳሻሽል ረድተውኛል" ይላል።

ሂውስተን አንድ ዓመት ከቆየ በኋላ ወደ ቴኒሲ፣ ጂዎርጂያ እና ፍሎሪዳ አቅንቷል። በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሴንትራል ፍሎሪዳ ሁለት ዓመት ቆይቷል።

"አንድ ሴኔጋላዊ ታዳጊ ነበርኩ። ቅርጫት ኳስ መጫወት የጀመርኩትም ከስድስት ዓመት በፊት ነበር። ኤንቢኤ ውስጥ ለመጫወት ብዙ ለፍቻለሁ። በጣም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል። ቅርጫት ኳስ ሕይወቴ ነው። አንድ ቀን እንኳን ሳልጫወት ባልፍ አዝናለሁ" ሲል ይናገራል።

ተያያዥ ርዕሶች