ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ለመሮጥ ዝግጅቱን አጠናቀቀ

ኤልዉድ ኪፕቾጌ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ኤልዉድ ኪፕቾጌ

ኬንያዊው የማራቶን ሯጭ ከ2 ሰዓት በታች የማራቶን ውድድርን ለማጠናቀቅ ቅድመ ዝግጀቱን አጠናቀቀ።

የማራቶን ክብረ-ወሰን ባለቤቱ ኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ የፊታችን ቅዳሜ በኦስትሪያ፤ ቪዬና የሚካሄደውን ማራቶን ከሁለት ሰዓት በታች ለመጨረስ ዝግጅቱን አጠናቋል።

በፈረንጆቹ 2018 በርሊን ማራቶትንን 2፡01፡39 በሆነ ፍጥነት በመጨረስ ነበር የዓለም ክብረ ወሰንን የሰበረው።

ቀነኒሳ 'ከሞት እንደመነሳት' ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ

ጉዬ አዶላ ማነው?

ከጥቂት ቀናት በፊት ቀነኒሳ በቀለ የበርሊን ማራቶንን ከኪፕቾጌ ክብረ ወሰን ሰዓት ሁለት ሰከንዶች ዘግይቶ በመግባት ማጠናቀቁ ይታወሳል።

ከሩጫው መድረክ ጠፍቶ የከረመው የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ በበርሊን ማራቶን ላይ ለውድድሩ ክብረወሰን ሁለት ሰከንዶች የቀሩት ውጤት አስመዝግቦ ካሸነፈ በኋላ ቀነኒሳ ስሜቱን ''ከሞት እንደመነሳት'' ነው ሲል ገልጿል።

ኪፕቾጌ ትናንት ምሽት ወደ ቪዬና ጉዞ ሲጀምር ፎቶግራፎችን በትዊተር ገጹ ላይ ለጥፎ ነበር።

ኬንያዊው አትሌት ኪፕቾጌ ትናንት ምሽት ነበር ድጋፍ የሚያደርጉለት እንግሊዛዊው ቢሊየነር ባዘጋጁለት የግል ጀት ልምምድ ከሚያደርግባት የኬንያዋ ኤልዶሬት ከተማ ወደ ቪዬና የበረረው።

ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች የመሮጥ እቅዱ ''INEOS 01፡59 ቻሌንጅ'' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

INEOS ለኪፕቾጌ በገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉት እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ ባለቤትነት የሚመራ የኬሚካል ኩባንያ ነው።

"ቪዬና ለውድድር ከተመረጠችባቸው ምክያቶች መካከል አንዱ፤ ለኪፕቾጌ ምቹ የሆነ የአየር ጸባይ ስለሚገኝባት ነው" ሲሉ የውድድሩ አዘጋጆች ተናግረዋል።

ኪፕቾጌ ከዚህ ቀደም በጣሊያን ማራቶን ከሁለት ሰዓት በታች ለመጨረስ ያደረገው ሙከራ ሳይሳከለት መቅረቱ ይታወሳል።

ተያያዥ ርዕሶች