በ45 ዓመቱ ዝግ ብሎ የሚራመድ በፍጥነት እያረጀ ነው-ጥናት

መንገደኞች በፍጥነት ሲራመዱ Image copyright Getty Images

በ40 ዓመትዎ ምን ያህል ፈጠን፣ ቀልጠፍ ብለው ይራመዳሉ? በርግጥ እንደ ጎረምሳ ዱብ ዱብ እንዲሉ አይጠበቅም። ደግሞም ዝግ ብለው የሚሄዱ ከሆነ ቀድመው እያረጁ መሆኑን ማሳያ ነው ይላሉ ተመራማሪዎች።

ሰዎች በ40ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ሆነው ፈጠን እያሉ የማይራመዱ ከሆነ አንጎላቸው እንዲሁም አካላቸው ምን ያህል እያረጀ እንደሆነ ማሳያ ነው ሲሉ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

ተመራማሪዎች ያደረጉት በቀላሉ እርምጃን በመለካት የእርጅናን መምጫ ፍጥነት መፈተሽ ነው።

ቲማቲም የወንዶችን የዘር ፍሬ ያበረታ ይሆን?

የወንድ ልጅ የዘር ፍሬን ሙቀት የለካው ምርምር ተሸለመ

ዝግ ብለው የሚራመዱ ሰዎች 'አካላቸው በፍጥነት እያረጀ ሲሆን፣ ፊታቸውም ከእድሜያቸው በላይ ማርጀታቸውን ያሳብቃል። አንጎላቸውም አነስተኛ ነው ' ሲሉ ይገልፃሉ።

የሕክምና ባለሙያዎች የእርምጃ ፍጥነትን የሚለኩት አጠቃላይ ጤንነትን ለማወቅ ነበር።

በተለይ ሰዎች እድሜያቸው ከ65 በላይ ሲሆን የጡንቻቸውን ጥንካሬ፣ የሳንባቸውን ሁኔታ፣ ሚዛንን መጠበቅ አለመጠበቅ፣ የአከርካሪ አጥንት ጥንካሬ እንዲሁም የዐይን ብርሃን ደህንነት ይፈተሻል።

ቀስ ብሎ መራመድ ከእድሜ መግፋት ጋር አብረው የሚመጡ፣ እንደ ዲሜንሺያ ያሉ የጤና ስጋቶች ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ብለዋል።

'እርጅና ብቻህን ና'

በዚህ ጥናት 1 ሺህ ኒውዝላንዳውያን ተሳትፈዋል። እድሜያቸው 45 መሆኑ ተረጋግጧል። ከዚያም የእርምጃቸው ፍጥነት ተለክቷል።

የጥናቱ ተሳታፊዎች የአካል ብርታታቸው፣ የአዕምሯቸው ብቃት እና ደህንነት እንዲሁም በልጅነታቸው በየሁለት ዓመቱ የአዕምሯቸው ብስለትና ምጥቀት መለኪያ ፈተና ወስደዋል።

"በዚህ ጥናት ያገኘነው ዝግ ብሎ የሚራመድ ከእድሜው ቀድሞ እያረጀ መሆኑን ነው" ይላሉ ይህንን ጥናት በበላይነት የመሩት ፕሮፌሰር ቴሪ ኢ ሞፊት።

ጋናውያኑን ያስቆጣው የስነ ወሲብ ትምህርት

ለሰው ልጅ ምርጡ ምግብ እንቁላል ይሆን?

እድሜያቸው 45 በሆናቸው ሰዎች መካከል የእርምጃ ፍጥነት ልዩነት መኖሩን የሚናገሩት ባለሙያው "ፈጣኑ ሰው 4 ሜትር በሰከንድ ነው የሚጓዘው" በማለት ይህ ሳይሮጥ መሆኑን ያሰምሩበታል።

በአጠቃላይ ቀስ ብሎ የሚራመድ "በፍጥነት እያረጀ" ለመሆኑ ምልክት ነው በማለት እንዲህ ዓይነት ሰዎች ሳንባቸው፣ ጥርሳቸው እንዲሁም በሽታ የመከላከል አቅማቸው በፍጥነት ከሚራመዱት ባሽቆለቆለ ይዞታ ላይ ይገኛል ብለዋል።

ተመራማሪዎቹ በ45 ዓመቱ ዝግ ብሎ የሚራመድን ሰው ከሦስት ዓመቱ ጀምሮ በሚደረግለት የተለያዩ የአዕምሮ ብቃት ፍተሻዎች፣ የቋንቋ ፈተናዎች ቀድሞ ማርጀቱና አለማርጀቱን መናገር ይቻላል ባይ ናቸው።

ይህም ቀድመው የሚያረጁ ሰዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ ምልክቱን ያሳያሉ ማለት ነው በማለት የሕይወት ዘይቤ ምርጫን ማስተካከል መፍትሔ መሆኑን ይመክራሉ።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ