"በርካታ አባላቶቻችን ስለታሰሩብን እነሱን ለማስፈታት እየተንቀሳቀስን ነው" እስክንድር ነጋ

አዲስ አበባ ፖሊስ አርማ Image copyright Addis ababa Police Facebook page

የአዲስ አበባ ፖሊስ በነገው ዕለት በከተማዋ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም ሲል አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ ለቢቢሲ እንደገለፁት፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች እሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሰልፍ እንደሚደረግ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሰልፉ ምክንያት የሚዘጉ መንገዶች መኖራቸውን ገለፀ በሚል የኮሚሽኑን አርማና የኃላፊዎችን ስም በመጠቀም የተላለፈው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ መስተዳደርና የባላደራው ምክር ቤት

በዛምቢያ ከካናቢስ እፅ ኬክ የጋገረው ተማሪ 50 ገጽ ሃተታ በመፃፍ ተቀጣ

17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ

አክለውም በነገው ዕለት ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ በመስቀል አደባባይ የሌለና ምንም የሚዘጋ መንገድ አለመኖሩን ተናግረዋል።

'የባላደራው ምክር ቤት' ትናንት በሰጡት መግለጫ ላይ ሕጋዊ መስፈርቶችን አሟልተው ለአዲስ አበባ መስተዳደር ጥያቄ ማቅረቡን ገልፀው ነበር።

በዚሁ መግለጫ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ ቢያቀርቡም መከልከሉም መፈቀዱም እንዳልተገለፀላቸው ተናግረው የነበሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፤ ነገር ግን ሕጉ እንደተፈቀደ ለማሳወቅ አያስገድድም በማለት 'ዝም በማለታቸው እንደተፈቀደልን ይቆጠራል' ብለው ነበር።

የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራው "ተስፋ የተጣለበት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ጅምር በመቀልበሱ ነው" ሲል አስታውቆ ነበር።

ከዚህ በፊት በተለያየ መንገድ ነገሮች እንዲስተካከሉ ድምፃቸውን ማሰማታቸውን፤ ነገር ግን ሰሚ በማጣታቸው ሁለተኛውን የሰላማዊ ትግል ስልት ለመጠቀም መገደዳቸውን ገልፀው ነበር።

በዚህም መፍትሄ ካላገኘን በቀጣይ መንግሥትን ወደሚያስገድዱ የሥራ ማቆም እና ሌሎች የትግል ስልቶች ለመግባት እንደሚገደዱም በመግለጫቸው ላይ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን እንዲሰጠን የደወልንለት 'የባለ አደራው ምክርቤት' ሊቀመንበር እስክንድር ነጋ "በአሁኑ ሰዓት በየቦታው በርካታ አባላቶቻችን ስለታሰሩብን እነርሱን ለማስፈታት እየተንቀሳቀስኩ ነው በዚህ ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት አልችልም" ሲል ተናግሯል።

በሌላ በኩል የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን የሰላም የኖቤል ሽልማትን በማስመልከት በነገው ዕለት በኦሮሚያ ክልል የደስታ መግለጫ ሰልፎች እንደሚካሄዱ የክልሉ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ማስታወቁን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

በመሆኑም ነገ እሁድ ጥቅምት 2፣ 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳዳሮች የደስታ መግለጫ ሰልፎች ይደረጋሉ ተብሏል።

በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለሚካሄደው ሰልፍም አስፈላጊው የፀጥታ ጥበቃ እንደሚደረግለት ተገልጿል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ