ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች አጠናቀቀ

ኢሊዩድ ኪፕቾጌ Image copyright Reuters

ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በመሮጥ የመጀመሪያው አትሌት ሆነ። ኪፕቾጌ ሩጫውን ለመጨረስ አንድ ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ40 ሰከንድ ፈጅቶበታል።

የ34 ዓመቱ ኬኒያዊ አትሌት 42.2 ኪሎ ሜትር ለመሮጥ የፈጀበት ሰዓት እንደ ዓለም ክብረ ወሰን እንደማይመዘገብለት የተገለጠ ሲሆን፣ ለዚህም ምክንያት ነው የተባለው የተጠቀማቸው አሯሯጮች፤ እየተፈራረቁ የሚያሯሩጡት አትሌቶች መሆናቸውና ለሁሉም ክፍት የሆነ ውድድር ባለመሆኑ ነው።

ኪፕቾጌ ውጤቱን አስመልክቶ ሲናገር "ይህ የሚያሳየው ማንም ሰው ሊያሳካው እንደሚችል ነው" ብሏል።

"አሁን እኔ አሳክቸዋለሁ፤ ከአሁን በኋላ ሌሎችም እንዲያሳኩት እፈልጋለሁ" ብሏል።

ኪፕቾጌን በሩጫ ይገዳደሩታል?

ከባህር ዳር - አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ዛሬም አልተከፈተም

ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ

ይሀ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና የአለም አቀፉን የማራቶን ክብረወሰን በአውሮፓዊያኑ 2018 ጀርመን በርሊን ላይ በሁለት ሰዓት ከ01 ደቂቃ 39 ሰከንድ በእጁ አስገብቶ ነበር።

የለንደን ማራቶንን አራት ጊዜ በማሸነፍ ስሙን የተከለው ኪፕቾጌ፤ ከድሉ በኋላ ባለቤቱ ግሬስን ተጠምጥሞ በመሳም የሀገሩን ባንዲራ ለብሶ በአሯሯጮቹ ተከብቦ ደስታውን ገልጧል።

ኪፕቾጌ በሚሮጥበት ወቅት ከፊት ከፊቱ በመሆን ሰዓቱን የሚጠቁመው መኪና የነበረ ሲሆን 100 ሜትሩን 17 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ በመሮጥ ለስኬት በቅቷል።

ኪፕቾጌን 42 አሯሯጮች ያሯሯጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የ1500 ሜትር ሻምፒዮናው ማቲው ቹንትሮ ዊትዝ፣ የ5000 ሜትር የመዳብ ባለቤቱ ፓል ቼሊሞና ኖርዌጂያን ወንድማማቾቹ ጃኮብ፣ ፍሊፕና ሄንሪክ ይገኙበታል።

እነዚህ አሯሯጮች እያረፉ ያሯሯጡት ሲሆን የ1500 እና የ5000 ዓለም ሻምፒዮና የሆነው በርናንርድ ላጋት የመጨረሻዎቹን ርቀቶች አሯሩጦታል።

ኪፕቾጌም "እነዚህ በዓለም አሉ የሚባሉ ዝነኛ አትሌቶች ናቸው፤ አመሰግናለሁ" በማለት፤ አክሎም "ይህንን ሥራ ስለተቀበሉ አመሰግናለሁ። ያሳካነው በጋራ ነው" ብሏል።

"የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ

17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ የእኛ ሠው በዶሃ

የኪፕቾጌ አሰልጣኝ አትሌቱ ልክ እንደ ሌላ ጊዜው የሚጠጣው ውሃ ከጠረጴዛ ላይ አንስቶ ከሚጠቀም ይልቅ በብስክሌት በመሆን ውሃና ኃይል ሰጪ ጄል ሲያቀብሉት ነበር።

እንዲህ ዓይነት እገዛ ግን በዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕግ መሰረት አይፈቀድም።

ኪፕቾጌ የሮጠበት ሥፍራ የተመረጠው የአየር ጠባዩ ምቹ ስለሆነ መሆኑ ተነግሯል።

ይህንን ሰዓት ለማሻሻል የተደረገውን ጥረት በገንዘብ የደገፉት እንግሊዛዊው ባለሀብት ሰር ጂም ራትክሊፍ በኩባንያቸው ፔትሮ ኬሚካልስ ስም ነው።

ናይክም አምስት የዓለማችን ፈጣን የማራቶን ሯጮች ብቻ ያደረጉት አዲስ ሞዴል ጫማ አበርክቶለታል።

የመጨረሻዎቹን ኪሎ ሜትሮች ያጠናቀቀበት ፍጥነት "አስደማሚ ነበር" ያሉት ራትክሊፍ ሲሆኑ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ በበኩላቸው " በዚህ ሙከራችን ሁሉም ነገር እንዳሰብነው ሄዷል" ብለዋል።

"ሁላችንንም ነው ያነቃቃው፤ በሕይወታችን አቅማችንን በመለጠጥ መፈተሽ እንደምንችል አሳይቶናል" ካሉም በኋላ "በስፖርቱ ዓለም ለሌሎች አትሌቶች ከሚያስቡት በተሻለ መሮጥ እንደሚችሉ ያሳየ፤ በሌላ ሕይወት መስክ ደግሞ ሌላ ከፍታ መውጣት እንደሚችል ያስተማረ ነው" በማለት ድሉን አሞካሽተውታል።

"በአጠቃላይ ታሪክ ተሠርቷል፤ የማይታመን ነገር ነው" ብለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ